በምሥራቅ ሐረርጌ በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር የአምስት ሴት ወጣቶች ሕይወት እንዲጠፋ ያደረገው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነ
*****************************************
በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር የ5 ሴት ወጣቶች ሕይወት እንዲጠፋ ያደረገው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ መወሰኑን የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ።
አብዱከሪም ጣሂር አብደላ የተባለው ግለሰብ ነዋሪነታቸው በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን፣ ጉርሱም ወረዳ፣ ዳይፈርስ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ነዋሪ የሆኑ ወጣት ሴቶችን በሕገ-ወጥ መንገድ በማስኮብለል ለሕልፈተ ሕይወት በመዳረጉ ቅጣቱ ተላልፎበታል።
በጎረቤት አገር በኩል ሳዑዲ ዐረቢያ ወስጄ በከፍተኛ ደመወዝ ሥራ እንድትቀጠሩ አደርጋለሁ በሚል ማታለያ በ2010 ዓ.ም በተለያዩ ቀናትና ወራት ከቀዬአቸው ካስኮበለላቸው 8 ወጣት ሴቶች ላይ ከእያንዳንዳቸው 3 ሺህ ብር ተቀብሏል።
ስልክ በመደወል እና ዘመድ አዝማድ ሳይሰማ ከአደጉበት ቀዬ ጨለማን ተገን በማድረግ ካስኮበለላቸው 8 ሴቶች መካከል በጀልባ መስጠም ምክንያት አምስቱ ሕይወታቸው ማለፉን ፍርድ ቤቱ መግለጹን ኢዜአ ዘግቧል።
No comments:
Post a Comment