A Yebbo Global Information Hub

EthioVibes Global

World travel, documents, money, auto, food, culture, history, sports, diaspora, business and technology.

Advertisement

የህወሓት ጦር ከአላማጣ ተሸንፎ ሲባረር በእስር ላይ የነበሩ 10,000 ያህል ሰዎችን ይዞ ሸሽቷል ተባለ።

Published
ህዳር 6፣2013

የህወሓት ጦር ከአላማጣ ተሸንፎ ሲባረር በእስር ላይ የነበሩ 10,000 ያህል ሰዎችን ይዞ ሸሽቷል ተባለ።

የመከላከያ ሰራዊት የራያ የአላማጣ ከተማን ከሕወሓት ነፃ አውጥቷል ሲልም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ ባወጣው መግለጫ ተናግሯል።

የከተማዋ ነዋሪዎች ዕድሜያቸው ከ14 ዓመት በላይ የሆኑ በርካታ የአካባቢው ወጣቶች በአጥፊው ኃይል ለጦርነት እንዳይመለመሉ በመፍራት አካባቢውን ለቀው መሰደዳቸውን ተናግረዋል ተብሏል።

መከላከያ ሠራዊት አላማጣን በቁጥጥር ስር ማዋሉ፣የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራው በሰላማዊ ዜጎች ላይ ተጽዕኖ እንዳያስከትል አስፈላጊው ጥንቃቄ ታክሎበት፣በውጤታማ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ያሳያል ሲል መግለጫው ተናግሯል።


Comments