Shop Amazon

Wednesday, November 18, 2020

ባለፉት 15 ቀናት የሀገርን ሰላም ለማደፍረስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ287 በላይ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌዴራል ፖሊስ ገለፀ

ባለፉት 15 ቀናት የሀገርን ሰላም ለማደፍረስ ባለፉት 15 ቀናት የሀገርን ሰላም ለማደፍረስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ287 በላይ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌዴራል ፖሊስ ገለፀ የነበሩ ከ287 በላይ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌዴራል ፖሊስ ገለፀ
******************

ባለፉት 15 ቀናት የፌዴራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባካሄዱት የተቀናጀ ኦፕሬሽን የሀገርን ሰላም ለማደፍረስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ287 በላይ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።

ከፅንፈኛው ሕወሓት እና ኦነግ ሸኔ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብው የተጠረጠሩት 287 ግለሰቦች ከጦር መሳሪያዎች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን ነው የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ያስታወቀው።

ፅንፈኛው የሕወሓት ቡድን በትግራይ ክልል በነበረው የሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት እና የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን ሲጠብቁ በነበሩ የፌዴራል ፓሊስ አባላት ላይ በፈፀመው ጥቃት ግድያ እና አፈና መፈፀሙን ኮሚሽኑ አስታውሷል።

ይህ ቡድን በመሀል ሀገርም ሊያደርስ የሚችለውን ማንኛውንም ጥቃት አስቀድሞ ለመከላከል ከቡድኑ ጋር ግንኙነት ያላቸውን አካላት ከእኩይ ተግባራቸው ለመግታት የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽኖች ላለፉት 15 ቀናት ዘመቻ ሲያካሂዱ ቆይተዋል።

በዚህም አንድንድ ድርጅቶች ከተቋቋሙበት ዓላማ ውጭ ለሀገር እና ለህዝብ ስጋት የሆነ ተግባር ላይ መሰማራታቸው እንደተደረሰበት ነው ኮሚሽኑ የገለፀው።

ለአብነት ሱር ኮንስትራክሽን በተባለው ድርጅት ላይ በተደረገ ህጋዊ ብርበራና ፍተሻ ለተለያዩ ዘመቻዎች የተዘጋጁ ተሽከርካሪዎች፣ የፀሀይ ሀይል ማመንጫ፣ ተንቀሳቃሽ እና ቋሚ ወታደራዊ ሬዲዮ መገናኛዎች በህንፃው ምድር ቤት ተሸሽጎ እንዳለ መያዙን የፌዴራል ፓሊስ ኮሚሽን በመግለጫ ላይ አስታውቋል።

በአጠቃላይ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከፅንፈኛው ሕወሓት እና ከኦነግ ሸኔ ጋር ግንኙነት አላቸው ብሎ የጠረጠራቸውን 287 ሰዎች በቁጥጥር ስር አውሎ ምርምራ እየተካሄደባቸው ነው ተብሏል።

በከተማዋ በተደረገ ብርበራ፣ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ፣ በፖሊስ አሰሳ እና ከግለሰቦቹ እና ከተጠረጠሩ ተቋማት 1 ሺህ 32 የተለያዩ ጠመንጃዎች፣ 131 የተለያዩ ሽጉጦች እና 46 ሺህ 39 ጥይቶች ተይዘዋል። 

እንዲሁም 14 ቦምቦች፣ 1 ፈንጂ፣ 5 ጂ ፒ ኤስ፣ 8 የጦር ሜዳ መነፀር፣ 5 ካቴና፣ 55 የክላሽ መጋዘን እና እጀታ፣ 1 ሺህ 339 የተለያዩ የኮሙኒኬሽን መሳሪያዎች፣ 845 ሺህ 434 የሀገር ውስጥ ገንዘብ እና 227 ሺህ 271 የተለያዩ የውጭ ሀገራት ገንዘቦች እንደተያዙ ነው ፓሊስ የገለፀው።

በተጨማሪም የተለያዩ የሰራዊት አልባሳት፣ ፓስፖርቶች፣ የውጭ ሀገር የስራ ፍቃድ ሰነዶች፣ በርካታ ገንዘብ ያዙ የባንክ ደብተሮች ፣ በሽጉጥ ላይ የሚገጠም የድምፅ ማፈኛ፣ የተለያዩ ኮምፒዩተሮች፣ ፀረ ታንክ መሳሪ እና ሌሎች መሳሪያዎች መያዛቸውም ተጠቁሟል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ከሚገኘው ዘመቻ ጋር ተያይዞ የጥፋት ሀይሉ ተላላኪዎች ሊጠቀሙባቸው የነበሩ የጦር መሳሪያዎች ሆን ብለው ዜጎች ላይ ጉዳት ሊያደርስ በሚችል መልኩ በየቦታው ጥለዋቸው የነበረ ቢሆንም ፓሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ሊያከሽፋቸው እንደቻለ ነው የተገለፀው። . Federal Police says it has arrested more than 287 individuals who were involved in disturbing the peace in the past 15 days.
 ******************

 The Federal Police Commission (FPC) said it has arrested more than 287 individuals who were involved in a joint operation by the Federal Police and the Addis Ababa Police Commission over the past 15 days.

 The Federal Police Commission has announced that 287 individuals suspected of links to the extremist TPLF and OLF have been arrested with weapons.

 The commission noted that the extremist TPLF had killed and abducted members of the Northern Command in the Tigray region and members of the Federal Police guarding various infrastructure.

 Federal and Addis Ababa police commissions have been campaigning for the past 15 days to prevent any possible attacks by the group inside the country.

 As a result, some organizations have been found to be engaged in activities that pose a threat to the country and the people, according to the commission.

 The Federal Police Commission (FPC) said in a statement that vehicles, solar panels, mobile and stationary military radios were found hidden in the basement of the building during a legal search of Sur Construction.

 In all, 287 people suspected of links to the extremist TPLF and OLF Shene are being investigated in various sub-cities of Addis Ababa.

 During the search, 1,32 different rifles, 131 pistols, and 46,399 rounds of ammunition were seized from the suspects, police, and individuals and suspects.

 Police also seized 14 bombs, 1 bomb, 5 GPS, 8 battle goggles, 5 cats, 55 cache and handguns, 1,339 various communication equipment, 845,434 domestic currency and 227,271 foreign currency notes.  Explained.

 They also seized a variety of military uniforms, passports, foreign work permits, banknotes, pistols, computers, anti-tank weapons and other equipment.

 At national level, weapons that were going to use the power of destruction associated with the Couriers campaign was panic everywhere in a manner that deliberately harm the citizens of this policy is to extend liyekeshifechewi according to the Society of receipt of the referral mentioned.

No comments:

Post a Comment