በሱዳን አብዬ የተሰማራው የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አመራሮችና አባላት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ አስመልክቶ ውይይት አካሄዱ
***********************************
በሱዳን አብዬ የተሰማራው የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አመራሮችና አባላት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ አስመልክቶ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የተገኙት በሱዳን አብዬ ሰሜን ቀጣና ላይዘን ኦፊሰር ብ/ጀ ዋኘው አለሜ በበኩላቸው፣ በሰሜን ዕዝ የሰራዊት አባላት ላይ የተፈፀመው ጥቃት እጅግ አሳዛኝና ሊወገዝ የሚገባው መሆኑን ገልፀው፣ በሰላም ማስከበር ተልዕኮ የተሰማራው ሃይል ተረጋግቶ ግዳጁ ላይ ትኩረት በማድረግና አንድነቱን በሚያተናክሩ ስራዎች ላይ መረባረብ ይገባል ብለዋል፡፡
የሻለቃው ዋና አዛዥ ኮ/ል ሐሰን አብደላ፣ መንግስት የጀመረውን ህግ የማስከበር ስራና ወንጀለኞችን ህግ ፊት ለማቅረብ እየወሰደ ያለው ህጋዊ እርምጃ ተገቢና የሚደገፍ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በቀጣይ ውስጣዊ አንድነታችንን የሚያጠናክሩ የግንባታ አቅጣጫዎችን በመከተልና ተልዕኳችን ላይ በማተኮር ቀሪ የግዳጅ ጊዜያቶችን ህዝባችንንና ሃገራችንን በሚያኮራ አኳኋን መፈፀም ይገባናል ብለዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎችም ጥቃቱን አውግዘው በጥቃቱ ሳንረበሽና ሳንደናገጥ ይበልጥ አንድነታችንንና ጓዳዊ ዝምድናችንን አጠናክረን የተሰጠንን ስራና ሃላፊነት በሚገባ በመወጣት የሰላም አምባሳደርነታችንን ማረጋገጥ አለብን ማለታቸውን ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
No comments:
Post a Comment