በአዲስ አበባ ወድቆ የተገኘ ቦምብ ፈንድቶ በአንድ ግለሰብ ላይ ቀላል የአካል ጉዳት አደረሰ
*************************************
በአዲስ አበባ ወድቆ የተገኘ ቦምብ ፈንድቶ በአንድ ግለሰብ ላይ ቀላል የአካል ጉዳት ማድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ህዳር 2 ቀን 2013 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት አካባቢ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው አድዋ ድልድይ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በአንድ ግለሰብ ላይ ቀላል ጉዳት እንደደረሰ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
በደረሰበት ጉዳት በምኒልክ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተለ የሚገኘው ግለሰብ ለመፀዳዳት ወደ ድልድዩ እንደገባና በማዳበሪያ የተጠቀለለ እቃ ተመልክቶ በእግሩ ሲረግጠው ከዚያ በኋላ ራሱን እንደሳተ ተናግሯል፡፡
የህገ-ወጡ ህወሓት ቡድን ተላላኪዎች በከተማችን የጥፋት ተግባር ለመፈፀም ያዘጋጇቸው የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በህብረተሰቡ ጥቆማና በፀጥታ ሀይሉ ክትትል በቁጥጥር ስር መዋሉን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
የፀጥታ ኃይሉ ጠንከራ እንቅስቃሴ እና ሕብረተሰቡ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመሆን እያደረገ ያለው ክትትል ያስጨነቃቸው የሽብር ቡድኑ ተላላኪዎች በአዲስ አበባ በተለያዩ ስፍራዎች በህዝቡ ላይ ጉዳት ለማድረስ በማቀድ ልዩ ልዩ የጦር መሳሪያዎችን በመጣል ጉዳት ሊያደርሱ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ ባለማወቅ ራሱን ለአደጋ እንዳያጋልጥ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡
እስካሁን ለተገኘው ውጤት የህብረተሰቡ አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልፆ በህገወጥ ቡድኑ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማስታወቁን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
A bomb explodes in Addis Ababa, injuring one person
*****************************************
Addis Ababa Police Commission says a bomb has exploded in Addis Ababa, injuring one person.
The Addis Ababa Police Commission announced that a person was slightly injured in the area known as Adwa Bridge, Yeka Sub-City, Woreda 7, around 2:00 am on November 10, 2013.
The man, who is being treated at Menelik Hospital, said he entered the bridge to defecate and saw a trampoline trampled on his feet and then fainted.
The commission said that various weapons prepared by the illegal TPLF operatives to carry out criminal activities in our city have been seized at the suggestion of the community and under the supervision of the security forces.
He called on the public to be vigilant so as not to inadvertently endanger the safety of the terrorists, who are worried about the security forces' hard work and the community's monitoring of the security forces.
No comments:
Post a Comment