Shop Amazon

Sunday, November 15, 2020

ስለ አማራ ልዩ ኃይል ጀብዱ የተሰጠ ምስክርነት

ስለ አማራ ልዩ ኃይል ጀብዱ የተሰጠ ምስክርነት (ከዒላማቸው ውጭ የመቱ ወታደሮች አላየሁም።)
           =====
ሀያ ሶስት ዓመታት በውጊያ ውስጥ ቆይቻለሁ። እነዚህን የመሰሉ ተዋጊዎች ግን አጋጥሞኝ አያውቅም። ክላሽንኮቭ ቁመው እንደስናይፐር ይተኩሳሉ። ከኢላማቸው ውጭ የመቱ ወታደሮች አላየሁም። የውጊያ ቀጠናቸው ከፊት ለፊቱ ግንባር በግራና በቀኝ ክንፍ ቢሆንም በፍጥነት ስለሚያጠቁ የመሃል ግባሩን ጭምር እነሱ ይሸፍኑት ነበር።

-ሌላው አስገራሚ ባህሪያቸው እጅግ ፈጣን ተዋጊዎች መሆናቸው ነው። ሶስት ቀናት ይፈጃሉ ተብለው የተገመቱትን ከሁመራ በስተ ምዕራብ እና በስተደቡብ ምዕራብ የሚገኙትን አራት ጠቃሚ ወታደራዊ ቦታዎችን በሰባት ስዓታት ብቻ የወገን ጦር ሊቆጣጠር የቻለው በእነሱ ታምራዊ የውጊያ ስልት ነበር።

- ከኤርትራውያን ጋር በዛላንበሳ እና በቡሬ ግንባር ተዋግቻለሁ። ከትግሬዎቹ ጋር አሁን የግንባር ጦርነት ውስጥ ገብተናል። ሁለቱም በፊት ለፊት ጦርነት ብዙም ባይሆኑ በደፈጣና በቆረጣ ውጊያ ድንቆች ናቸው ።
ዐማሮቹ ግን በሁሉም የውጊያ ዓይነቶች ፍጹም ተወዳዳሪ የላቸውም።

-አስቸጋሪ ይሆናሉ ተብለው በተገመቱ ግንባሮች ለመሰለፍ አያመንቱም። እንደውም ጀብዱ ለመፈፀም ካላቸው ፅኑ ፍላጎት የተነሳ የጠላት ጦር ይበረታባቸዋል የተባሉትን ምሽጎች ለመደርመስ ይሽቀዳደማሉ። ጦርነቱ ጋብ ሲል ወደ ማታ የሰው ኃይል ስምሪትና ድልድል ቆጠራ ስናደርግ ከእነሱ ወገን ጥቂትም ቢሆን የጎደለ የለም። ወታደራዊ ስልጠና ብቻውን እንዲህ አያደርግም ከትውልድ የሚተላለፍ አንዳች ድፍረትና ብልሃት ቢኖር እንጅ ብየ አስባለሁ።

-ስለ ዐማራ ልዩ ኃይል እና ስለ ዐማሮቹ ጀግንነት የምገልፅበት ቃላት ባይኖረኘም በቻልኩት አቅምና ባገኘውት አጋጣሚ ለሁሉም ከምንመሰክረው የጦር ሜዳ ውሎየና ከወታደር ታሪኬ አንዱ ይሄው ነው። ኢትዮጵያ ከሁለት ሽህ ዓመታት በላይ ታፍራና ተከብራ የኖረችበት አንዱ ሚስጥር ይሄው ነው።
*
በወልቃይት ሁመራ ግንባር ከዐማራ ልዩ ኃይል ና ሚሊሻ ጋር የተሰለፈ የደቡብ ኢትዮጵያ ተወላጅ የመከላከያ መኮንን ስለ ዐማራ ልዩ ኃይል ጀግንነት ከሰጠው የዓይን ምስክርነት።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ Belete Kassa Mekonnen

No comments:

Post a Comment