የአማራ ልዩ ኃይል ሰራዊት የጀርባ አጥንት:- ኮሎኔል ኢትዮጵያ ገብረመድህን
==========================
ይህ ብዙ ያልተነገረለት ጀግናል የአማራ ልዩ ኃይል ካደራጁት ወታደራዊ አዛዦች ውስጥ ግንባር ቀደሙ ነው:: የአማራ ልዩ ኃይል ሰራዊት ሰልጠና መምሪያ ዋና አዛዥ:-ኮሎኔል ኢትዮጵያ ገብረመድህን
ትንሽ ስለ ስል ኢትዮጵያ ገብረመድህን::
ኢትዮጵያ ተወልዶ ያደገው በሰሜን አማራ ደባርቅ አውራጃ በየዳ ወረዳ ልዩ ስሙ ፍየል ውሃ ነው::
1976 ዓ.ም በፀረ ደርግ ትግሉን ወቅት ከጏደኞቹ ጋር በመሆን በዳባት አውራጃ በተለያዩ ቦታዎች በመንቀሳቀስ የኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄን ተቀላቀለ ከዚያም እጅግ የታወቀ ተኳሽ በመሆኑ የብሬን( መትረጌስ) ተኳሽ ሁኖ ተመድቦ እስክ ብርጌድ አዛዥነት ድረስ አገልግሏል::
በ1987 ዓ.ም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሲቋቋም የብርጌድ አዛዥ ሆኖ ተመደበ:: በ1990ና በ1992 ዓ.ም በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት በ15 ክፍለ ጦር የብርጌድ አዛዥ በመሆን በተሰነይና በባሬንቱ ግንባር ጀግንነት ከፈፀሙ ተዋጊና አዋጊዎች መካከል ግንባር ቀደሙ ነው::
ኢትዮጵያ የ43ኛ, 44ኛና 26ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ በመሆን አገልግሏል::
በ1997 ዓ.ም የ26ኛ ክፍለ ጦር በጎንደርና አካባቢ ያለውን ጦር ኢትዮጵያና ጏደኛው ሊተናል ኮሎኔል መላይ አማረ( ትህነግ) ክፍለ ጦሯን ይመሯት ነበር:: በወቅቱ ጎንደር ውስጥ የመላይ ጏደኛ መሳሪያ ዘርፎ ሲሸጥ በመገኘቱ ኮሎኔል ኢትዮጵያና በወቅቱ የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ የነበረው ጌታቸው ጀንበር ግለሰቡን ያስሩታል:: ከዚያ መላይና ጏደኞቹ የታሰረውን ትግሬ ያስፈቱታል:: ከዚያም ኢትዮጵያ ለምንድን ነው እነ ጌታቸው ያሰሩትን የምታስፈቱት በማለቱ በወቅቱ የምዕራብ ዕዝ አዛዥ የነበረው ብርጋዴር ጀኔራል አብርሃ ወልደማሪያም( ኳርተር) ኮሎኔል ኢትዮጵያን ቅንጅት ነህ ብሎ ግምግሞ የመላይን ጏደኛ( ትህነግ) ከእስር ቤት ያስፈታና ኢትዮጵያን ያለ ምንም ጡረታ ባዶ እጁን ያባርረዋል:: ኢትዮጵያ ምንም ማድረግ ስላልቸለ ተባሮ ጊዜ ሲጠባበቅ ኖረ
በ2010 ዓ.ም ትህነግ ከአዲስ አበባ ስትባረርና የአማራ ልዩ ኃይልን ለማደራጀት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጥሪ ሲያቀርብ ቀድመው ጥሪውን ተቀብለው ከመጡት ኮሎኔሎች መካከል ኢትዮጵያ አንዱ ነው:: የአማራ ልዩ ኃይል ሰራዊት አባት ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም::
በአሁኑ ሰዓት ድምፁን አጥፍቶ እየሰራ ነው:: ማህበራዊ ሚዲያ ያላነገሳቸው ጀግኖች የአማራ ህዝብ ባለውለታ ናቸው::
ክብር ለሚገባው ብቻ ክብር እንስጥ!
ከቢኒያም ዘሚካኤል ገፅ የተወሰደ
No comments:
Post a Comment