Shop Amazon

Monday, November 16, 2020

የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ በኢትዮጵያ ድርድር እንዲደረግ የጠየቁበትን የትዊተር መልዕክት አጠፉ

የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ በኢትዮጵያ ድርድር እንዲደረግ የጠየቁበትን የትዊተር መልዕክት አጠፉ። ፕሬዝዳንቱ ከምክትል ጠቅላይ ምኒስትር ደመቀ መኮንን ከተነጋገሩ በኋላ "ጦርነት በኢትዮጵያ ለአጠቃላይ አኅጉሩ የከፋ ምስል ይሰጣል። ድርድር ተደርጎ ግጭቱ ሊቆም ይገባል። አለበለዚያ ወደ አላስፈላጊ የሰው ሕይወት መጥፋት ይመራል። ኤኮኖሚውንም ያሰናክላል" ብለው ነበር። 
ሙሴቬኒ ከምክትል ጠቅላይ ምኒስትር ደመቀ መኮንን አብረው ሲጓዙ እና ሲነጋገሩ የሚያሳዩ ምስሎች እና ፕሬዝዳንቱ የጻፏቸው መልዕክቶች አሁንም በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ቢገኙም "ድርድር ሊደረግ ይገባል" የሚል መልዕክት ያዘለው ግን ተለይቶ ጠፍቷል።

No comments:

Post a Comment