ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ሕዝቡ በንቃትና በተደራጀ መንገድ አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ አቀረቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሕዝቡ በንቃትና በተደራጀ መንገድ አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ አቀረቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው የጁንታው ፀሐይ እየጠለቀች ነው ብለዋል ።
ይሄንን መርዶ ጁንታው በቁሙ እንደተረዳው ነው የገለፁት።
ጁንታው አሁን የሚይዘውን የሚጨብጠውን የሚያጣበት ጊዜ በመሆኑ በጣዕር መንፈስ በየቦታው የመጨረሻውን የጥፋት ድግስ ይደግስ ይሆናልም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ።
በመሆኑም ሕዝቡ በንቃትና በተደራጀ መንገድ አካባቢውን እንዲጠብቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል ።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ወገኖች በየአካባቢው ምንም ዓይነት አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳይደርስባቸው ሁሉም የወንድሞቹ ጠባቂ እንዲሆንም መልዕክት አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያ ጠላት ስግብግቡ ጁንታ መሆኑን በመጥቀስም የትግራይ ሕዝብ እንደሌላው ሕዝብ በጁንታው መከራ ያየ ሕዝብ መሆኑንን አስታውቀዋል።
ጁንታው ለፍርድ እንዲቀርብ የትግራይም ሕዝብ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር አብሮ እየተዋጋ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ህዝቡም አካባቢዬን እጠብቃለሁ፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ የመከራ ቀንበር እሰብራለሁ፤ ጁንታውን ለፍርድ አቀርባለሁን ቃል ኪዳኑ ሊያደርግ እንደሚገባም ገልፀዋል ።
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ

Prime Minister Abiy Ahmed called on the people to protect the area in an active and organized manner.
Prime Minister Abiy Ahmed called on the people to protect the area in an active and organized manner.
The Prime Minister said on his social media page that the sun is setting.
He asserted that his confession had been obtained through torture.
"It is time for the junta to lose its grip on power," he said.
He called on the people to be vigilant and organized in order to protect the environment.
In this regard, he also conveyed a message to the people of Tigray to be the guardians of all his brothers so that they are not harmed in any way.
He said the enemy of Ethiopia is the greedy Junta, adding that the people of Tigray are suffering like the other people.
He said the people of Tigray are fighting alongside the Defense Forces to bring Junta to justice.
I will protect my people; I will break the yoke of the Ethiopian people; "I will bring Junta to justice," he said.
No comments:
Post a Comment