Shop Amazon

Friday, November 6, 2020

Ethiopia, Austria sign air service agreement

ኢትዮጵያ እና ኦስትሪያ የአየር በረራ አገልግሎት ስምምነት ተፈራረሙ 
********************* 

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግሥት ከኦስትሪያ ፌዴራል መንግሥት ጋር እ.ኤ.አ. ታኅሣሥ 10/2013 በአጭር ፊርማ የነበረውን የአየር በረራ አገልግሎት ስምምነት የተሻለ የበረራ ምልልስ እና የሕግ መሠረት በሚሰጥ መልኩ በትላንትናው ዕለት አዲስ አበባ ላይ በተካሄደ የምክክር ስብሰባ አሻሽሎ ተፈራረመ። 

ስምምነቱን በኢትዮጵያ በኩል የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኮ/ል ወሰንየለህ ሁነኛው እና የኦስትሪያ ፌዴራል መንግሥት በኩል ደግሞ በኢትዮጵያ የኦስትሪያ አምባሳደር ሚስተር ሮላንድ ሐውሰር ተፈራርመዋል። 

የስምምነቱ በሙሉ ፊርማ ደረጃ መጠናቀቅ ለብሔራዊ አየር መንገዱ የበረራ መብቶች ሕጋዊ መሠረት የሚሰጥ መሆኑን እና የበረራ ምልልሱንም በየጊዜው በሚኖረው የአየር ትራፊክ ገበያ ልክ ማሳደግ የሚያስችል መሆኑን በባለሥልጣኑ የኢኮኖሚክ ሬጉሌሽንና ስትራተጂክ አመራር ዳይሬክተር አቶ እንደሻው ይገዙ ገልጸዋል። 

እንደ አቶ እንደሻው ገለፃ ስምምነቱ ተወካይ አየር መንገዶች ከበረራ የሚያገኙትን ገቢ ከተደራራቢ ግብር ነፃ የሚያደርግ፣ ከአዲስ አበባ እና ቪዬና ከተሞች በተጨማሪ በከተሞቹ መካከል እና ባሻገር ባሉ ሌሎች መዳረሻ ከተሞች የበረራ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል እና አየር መንገዶችን በሽርክና እንዲሠሩ የሚፈቅድ ነው። 

ስምምነቱ ኢትዮጵያ ከኦስትሪያጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት በበለጠ የሚያጠናክር እና በሀገራዊው የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ ዓለም አቀፍ የበረራ መዳረሻዎችን ቁጥር ማሳደግ በሚል የተጣለውን ግብ ስኬታማነት የሚያረጋግጥ ይሆናል። 

ከዚህ በተጨማሪም የአየር ትራንስፖርቱ ንግድ እና ኢንቨስትመንትን በማበረታታት፣ የወጪ ንግዱን በመደገፍ፣ ቱሪዝምን በማስፋፋት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራና በውጭ ምንዛሪ ግኝት ያለውን ሚና እንደሚያጎለብት ይታመናል ሲል የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን አስታውቋል። 
Sourcev EBS

No comments:

Post a Comment