*********************
34 የሕወሓት የፋይናንስ ተቋማትን የባንክ ሂሳብ ቁጥር ማሳገዱን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታውቋል፡፡
ሱር ኮንስትራክሽን፣ ጉና የንግድ ስራዎች ፣ ትራንስ ኢትዮጵያ፣ መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪንግ፣ ሰላም የህዝብ ማመላለሻ ማህበር፣ ሜጋ ማተሚያ፣ ኢፈርት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እንዲሁም ኢፈርት ኤሌክትሪካል ቢዝነስ ገንዘባቸው ከታገደባቸው ተቋማት መካከል ናቸው።
ኢዛና ማእድን ልማት፣ቬሎሲቲ አፕሪዝ፣ መሶበ የግንባታ ስራዎች፣ ሳባ ስቶን፣ ኤፍ ኤክስፕረስ፣ ሜጋኔት ኮርፖሬሽን፣ ካትሪና ሼባ ታነሪናም በእገዳው ተካትተውበታል።
ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ስራ ላይ ካዋላቸው አዋጆች መካከል አዋጅ ቁጥር 882/2007 እና ሌሎች አዋጆችን መሰረት በማድረግ ነው እገዳውን የጣለው።
በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በወንጀል የተገኘ ሐብት ማስመለስ ዳይሬክተር ጄኔራል ዓለምአንተ አግደው እንደተናገሩት በእነዚህ ተቋማት ስም በሁሉም ባንኮች የተቀመጡ የሂሳብ አካውንቶች እገዳ ተጥሎባቸዋል።
ጠቅላይ አቃቤ ህግ እነዚህ ተቋማትን በኢትዮጵያ የሚፈጸሙ ዘር ተኮር ጥቃትቶችን እና የሽብር ተግባራትን እና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ ከሚሰሩ አካላት ጋር በመመሳጠር እና ግንኙነት በመፍጠር ፋይናንስ በማድረግ እንዲሁም በሙስና ወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል እንደጠረጠራቸው ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
ከ34 ተቋማት መካከል ትምዕት እና መሶበ ሲሚንቶ ከድምጸ ወያኔ መገናኛ ብዙሃን ጋር ሼር እንዳላቸው መረጋገጡን ከጠቅላይ አቃቤ ህግ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በዚህ መሰረት ድምጸ ወያኔ ከትምዕት 8 ሚሊዮን ብር ብሎም ከመሶበ ሲሚንቶ 61 ሚሊዮን ብር በላይ የአክሲዮን ድርሻ እንዳለው ተቋሙ ገልጿል።
በዚህም ድምጸ ወያኔ አሁን ላይ በኢትዮጵያ እያካሄደ ባለው ግጭት የገንዘብ ድጋፍ ከእነዚህ ተቋማት እንደሚያገኝ በሰነድ መረጋገጡን ኃላፊው ተናግረዋል።
በአጠቃላይ በፋይናስ ተቋማቱ ላይ እግዱ አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት ድርጅቶቹ ሀብታቸውን ለማሸሽ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሆኑ በቂ ማስረጃ የቀረበ በመሆኑ፣ ንበረቶቹ ሳይሸሹ ተገቢውን ቁጥጥር በማድረግ ውሳኔ እስኪሰጥባቸው ማቆየት ተገቢ መሆኑ ስለታመነበት ነው ተብሏል፡፡
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በወንጀል የተገኘ ሀብት ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል የመመርመር እና ሀብትን የማስመለስ ስራውን እስኪያጠናቅቅ ድረስ የታገዱት ንብረቶች እንዳይጎዱ እና እንዳይባክኑ ጠብቆ የሚያቆይ የንብረት አስተዳዳሪ የሚሾም ሲሆን አስተዳዳሪው ስራውን ተቀብሎ ማስተዳደር እስኪጀምር ድረስ የድርጅቶቹ አስተዳዳሪዎች ንበረቱን በሚገባ የመጠበቅ ኃላፊነት እንዳለባቸውም ተገልጿል፡፡
የታገዱት ድርጅቶች ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘሩት ናቸው
1. ሱር ኮንስትራክሽን
2. ጉና የንግድ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር
3. ትራንስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
4. መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
5. ሰላም የህዝብ ማመላለሻ አክሲዮን ማህበር
6. ሜጋ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
7. ኤፈርት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
8. ኤፈርት ኤሌክትሪካል ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
9. ኤፈርት ዲዛይን እና ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር
10. ኢዛና ማዕድን ልማት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
11. ቬሎሲቲ አፖራልዝ ካምፓኒስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
12. መሰቦ ቢውልዲንግ ማቴሪያል ፕሮዳክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር
13. ሳባ ዳይሜንሺናል ስቶን ኃ/የተ/የግ/ማህበር
14. መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ
15. ሼባ ታነሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
16. ኤ.ፒ ኤፍ
17. ሜጋ ኔት ኮርፖሬሽን
18. እክስፕረስ ትራንዚት ሰርቪስ
19. ደሳለኝ ካትሪናሪ
20. ሼባ ታነሪ ፋክተሪ አክሲዮን ማህበር
21. ህይወት አግሪካልቸር መካናይዜሽን
22. ህይወት እርሻ ሜካናይዜሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር
23. አልመዳ ጋርመንት ፋክተሪ
24. መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ
25. ደደቢት ብድርና ቁጠባ አክሲዮን ማህበር
26. አዲስ ፋርማሲቲካልስ ፕሮዳክሽን
27. ትግራይ ዴቨሎፕመንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
28. ስታር ፓርማሲቲካልስ ኢፖርተርስ
29. ሳባ እምነበረድ አክሲዮን ማህበር
30. አድዋ ፍሎር ፋክተሪ
31. ትካል እግሪ ምትካል/ ትግራይ/ ት.እ.ም.ት/
32. ብሩህ ተስፋ ፕላስቲክ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
33. ደሳለኝ የእንስሳ መድኃኒት አስመጪና አከፋፋይ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
34. ማይጨውፓርትክል ቦርድ ፋክተሪ
በጥላሁን ካሳ
The FDRE Attorney General announces the suspension of TPLF 34 financial institutions
*********************
The Attorney General of the Federal Democratic Republic of Ethiopia (FDRE) has announced that he has suspended the bank accounts of 34 TPLF financial institutions.
Sur Construction, Guna Business, Trans Ethiopia, Mesfin Industrial Engineering, Selam Public Transport Association, Mega Printing, Effort Private Limited, and Effort Electric Business are among the companies banned.
Izana Mining Development, Velocity Apris, Mesobe Construction, Saba Stone, F Express, Magnet Corporation, Katherine and Sheba Tannerina are also included in the ban.
Proclamation No. 882/2007 and other proclamations imposed by the Attorney General were suspended.
According to the Federal Attorney General, Director of Criminal Recovery, Crime accounts held in all banks in the name of these institutions have been suspended.
He said the attorney general suspected that these institutions were involved in racist and terrorist activities in Ethiopia and by financing and co-operating with those working to overthrow the constitutional order, as well as money laundering.
According to the Attorney General, out of 34 institutions, Timet and Mesobe Cement have been confirmed to have shared with the TPLF media.
According to the institute, the TPLF has a share of 8 million birr and more than 61 million birr from Mesobe Cement.
He said the TPLF has received financial support from these institutions in the ongoing conflict in Ethiopia.
In general, the reason for the ban on financial institutions is that there is ample evidence that the companies are trying to misappropriate their assets, and it is believed that it is appropriate to keep the assets under control and wait for a decision.
The Attorney General of the Federal Democratic Republic of Ethiopia (FDRE) will appoint an asset manager to ensure that the frozen assets are not damaged or wasted until the Director General of the Criminal Assets Recovery Directorate completes its investigation and recovery.
The banned organizations are listed below
1. Sur Construction
2. Guna Business Pvt
3. Trans Ethiopia PLC
4. Mesfin Industrial Engineering Plc
5. Selam Public Transport Share Company
6. Mega Printing Plc
7. Effort Plc
8. Effort Electrical Business Plc
9. Effort Design and Construction Plc
10. Izana Mining Development Plc
11. Velocity Apocalypse Company Plc
12. Mesebo Building Material Production Plc
13. Saba Dimensional Stone Plc
14. Mesfin Industrial Engineering
15. Sheba Tanari Plc
16. APF
17. Mega Net Corporation
18. Express Transit Service
19. Desalegn Catherine
20. Sheba Tanner Factories SC
21. Life Agricultural Mechanization
22. Life Agricultural Mechanization Plc
23. Almeda Garment Factory
24. Mesobo Cement Factory
25. Dedebit Credit and Savings Corporation
26. New Pharmaceutical Productions
27. Tigray Development Plc
28. Star Pharmaceuticals Eporters
29. Saba Marble Stock Company
30. Adwa Floor Faculty
31. Tkal Egri Mitkal (Tigray)
32. Bright Hope Plastic Plc
33. Desalegn Veterinary Import and Distribution PLC
34. Matchboard Board Faculty
By Tilahun Shadow
No comments:
Post a Comment