Shop Amazon

Saturday, November 7, 2020

The Federal Government is working to uphold the rule of law in accordance with the country's constitution, the Prime Minister's Office said

የፌዴራል መንግስት በአገሪቱ ሕገ መንግስት መሰረት የሕግ የበላይነት የማስከበር ስራ እየሰራ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ገለጸ
********************************

 ህወሃት የአገሪቱን ሕገ መንግስት በመጣስ በመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የፌዴራል መንግስት በአገሪቱ ሕገ መንግስት መሰረት የሕግ የበላይነት የማስከበር ስራን እየሰራ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ገልጿል፡፡

አሁን ስልጣን ላይ ያለው መንግስት ከሁለት ዓመታት በፊት ወደ ስልጣን መምጣቱን ተከትሎ አገሪቱን በሕግ ሳይሆን በጭቆና ለ27 ዓመታት ሲገዛ የነበረው ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራት /ህወሃት/ ሰላማዊ ዜጎችን እንደ ጋሻ በመጠቀም በመቐለ ከተማ ከፍትሕ ሸሽተው መቆየቱን ጽ/ቤቱ ገልጿል፡፡

ቡድኑ  ባለፉት ሁለት ዓመታት ለተለያዩ ቡድኖች ድጋፍ በማድረግ አገርን የማተራመስ ተግባር ላይ ተጠምዶ የነበረው ቢሆንም፣ የፌዴራል መንግስት ሁኔታውን በትዕግስት ሲከታተል መቆየቱ ተገልጿል፡፡

የፌዴራል መንግስቱ ህወሃት በአገሪቱ ውስጥ የተፈጠረው የሪፎርም አካል እንዲሆን የውይይት፣ የድርድርና የጋራ መግባባት እድሎች ተከፍተው ሁሉም የሰላም አማራጮች የተጠቀመ ቢሆንም ቡድኑ ባሳማራቸው የጥፋት ኃይሎች  አማካኝነት በምዕራብ ጎንደር፣ ሻሸመኔ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ ቤኒሻንጉል፣ ጉራ ፈርዳ፣ እንዲሁም በቅርቡ በምዕራብ ወለጋ ጥቃት መፈጸሙን ጽ/ቤቱ ገልጿል፡፡

መንግስት በገለልተኛ አካላት በኩል ድርድር እንዲደረግ ከፍተኛ ጥረት ቢያደርግም ህወሃት ሕገ ወጥ ምርጫ በማድረግና የፌዴራል መንግስቱን እንደ ሕገ ወጥ አካል በመቁጠር ለፌዴራል መንግስቱ እውቅና እንደማይሰጥ ገልጸ ነበር ተብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም ቡድኑ በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መሰነዘሩን ተከትሎ የፌዴራል መንግስት የመከላከያ ሰራዊት ራሱን እንዲከላከል እንዲሁም በአገሪቱ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር ትእዛዝ ማስተላለፉ ተገልጿል፡፡

 በትግራይ ለ6 ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያስፈፅም በኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሰብሳቢነት የሚመራና አግባብነት ካላቸው አካላት የተውጣጡ አባላት ያሉት ግብረ ኃይል በዚህ አዋጅ መቋቋሙ የተገለጸ ሲሆን፣ ግብረ ሀይሉ አስፈላጊ ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ፦
• ፖሊስን ጨምሮ ማንኛውንም የፀጥታ ሃይል ትጥቅ እንዲፈቱ ማድረግ፣ 
• የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ጨምሮ አስፈላጊ ናቸው ብሎ ያመነባቸው ሌሎች እንቅስቃሴዎች 
ላይ ገደብ መጣል፣ 
• የሰአት እላፊ ገደብ የማውጣት፣ 
• የጦር መሳሪያ እንቅስቃሴዎችን የማስቆም፣
• የመገናኛ ዘዴዎች እንዲቋረጡ የማድረግ፣ እንዲሁም 
• ህገ ወጥ በሆነ ተግባር ላይ ተሳትፈዋል ብሎ የጠረጠራቸውን ግለሰቦችና ቡድኖች የመያዝና የማቆየት ኃላፊነት ይኖረዋል መባሉን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡።

No comments:

Post a Comment