አዲስዓለም ባሌማ (ዶ/ር) በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አስታወቁ
**************
በህግ ሲፈለጉ ከነበሩት የጁንታው ሕወሓት ቡድን አባላት መካከል አንዱ የሆኑት አዲስዓለም ባሌማ (ዶ/ር) በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታወቁ።
የተቀሩትን የጁንታውን አባላት ለመያዝ የሚደረገው አሰሳ መቀጠሉን የገለጹት ቃል አቀባዩ፣ መከላከያ ሠራዊቱ እና ፌዴራል ፖሊስ የመሸጉበትን ስፍራዎች የደረሱበት በመሆኑ በቅርብ ቀናት፣ ቢበዛ በሳምንታት ውስጥ በቁጥጥር ስር የሚውሉ መሆኑን ተናግረዋል።
መንግሥት በትግራይ ክልል በማከናወን ላይ ስለሚገኘው ወንጀለኞችን አድኖ ለህግ የማቅረብ እና መልሶ ግንባታ ስራዎችን አስመልክቶ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት እና የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በጋራ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።
Ambassador Redwan Hussein announces the arrest of Addisalem Balema (Dr)
**************
Addis Ababa Alem Balema, one of the wanted members of the Junta TPLF, has been arrested, Ambassador Redwan Hussein, Spokesman for the State of Emergency Proclamation, told reporters today.
He said the search for the remaining members of the junta was continuing and that they would be arrested in the coming days, at most weeks, as the army and the federal police had reached their hideouts.
The State of Emergency Proclamation and the National Disaster Risk Management Commission (NDRMC) briefed the media on the ongoing operation in Tigray State to hunt down and prosecute criminals.
No comments:
Post a Comment