By Amdemariam Ezra - ግልባጩ:- ለኤርትራን ፕሬስ (Eritrean Press)
በፎቶው የምትመለከቱት ምስል በሁመራ ከተማ ለንጹሃን የአማራ ተወላጆች በትህነግ ተጨፍጭፈው በጀምላ ሊቀበሩበት ተዘጋጅቶ የነበረ ጉድጓድ ነው።ይህን ጉድጓድ በዐይኔ አይቼ ምስሉን በካሜራዬ ይሄው አስቀርቸዋለሁ።ይሁን እንጂ ጉድጓዱ እንዲህ አፉን ከፍቶ ተጀምሮ የቀረው ከፈጣሪ በታች በኤርትራዊያን ወንድማዊ ክንድነት ነው።
ትህነግ የጨፈጨፉት የመከላከያ ሰራዊቱን ብቻ አይደለም።ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም በማይካድራ (ካድራ ውሃ) የአማራ ተወላጆችን በዘራቸው መርጠው ከ1200 በላይ ንጹሃንን ጨፈጨፉ።የማይካድራው ዘግናኝ ጭፍጨፋ በሁመራ ከተማም ሊደገም ነበር።
የንጹሃን ማረጃዎች ተስለዋል።ከ1000 በላይ ሊታረዱ የታቀደላቸው የአማራ ተወላጆች ተመዝግበዋል።ሁመራ በሄድኩበት ወቅት ይህን አረጋግጫለሁ።ከእርድ የተረፉ በርካታ ወጣቶችን አነጋግሪያለሁ።በስም ዝርዝር የተያዙት ንጹሃን የአማራ ተወላጆች በጅምላ ከተጨፈጨፉ በኋላ ሁመራ ላይ በስካባተር የምድር ከርስ ተቀርድዶ ለጅምላ መቃብርነት የታሰቡ ሁለት ጉድጓዶችን በዐይኔ በብረቱ ተመልክቻለሁ።እንዲያውም በአንደኛው የጅምላ መቃብር በሁመራ ከተማ ትህነግ በግፍ ከረሸናቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል ሁለቱ ተቀብረውበታል።መቃብራቸውን ዐይቻለሁ።
ታዲያ የማይካድራው (የካድራ ወንዙ) አይነት ዘግናኝ ጭፍጨፋ እንዴት ሁመራ ላይ ከሸፈ? ከ1000 በላይ ንጹሃን የአማራ ተወላጆችን ማን ከጅምላ እርድ ታደጋቸው?
ልብ በሉ እንግዲህ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣የአማራ ልዩ ኃይል፣የአማራ ሚሊሻና ፋኖ ሁመራን ገና አልተቆጣጠረም።ይህን ክፍተት በፍጥነት ለመጠቀም የትህነግ አሸባሪዎች እየተጣደፉ ነው።የአማራ ተወላጆችን እንዲያርዱ ለተደራጁት የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች ገጀራ መታደል ተጀምሯል።የትህነግ ፖሊስ፣ልዩ ኃይልና ሚሊሻ መሳሪያውን አቀባብሎ በተጠንቀቅ ቁሟል።በማይ ካድራው (በካድራ ወንዙ) ጭፍጨፋ እርር ድብን እያል፣የኤርትራ ወታደሮች በደንበር ባይኖሩ ኑሮ ሃዘናችን እጥፍ ድርብ ይሆን ነበር።ሁመራም በንጹሃን የደም ጎርፍ ትታጠብ ነበር።
ነገር ግን የማይካድራው ጭፍጨፋ በሁመራ ሊደገም መሆኑን የኤርትራ መንግስት ደህነነቶች ሰሙ።መረጃው የደረሰው ዘግይቶ ነው።ጨፍጫፊዎች ገጀራ ከጨበጡ በኋላ ማለት ነው።ግን የኤርትራ ወታደሮች የሃዛችን እጥፍ ድርብ እንዳይሆን ፈጥነው ደረሱ።ከ1000 በላይ የንጹሃንን ነብስ ታደጉ።ለኤርትራ ደህንነቶች መረጃው ዘጊይቶ ቢደርስም ጊዜ አላጠፉም።በቅጽበት የጭፍጨፋው መረጃ ለኤርትራ መንግስት የበላይ ባለስልጣናት እንዲደርስ አደረጉ።ባለስልጣናቱም ሴኮንድ አላባከኑም።የኤርትራ ወታደር ከኤርትራ ግዛት ሁኖ ወደ ሁመራ ሞርተሩን ያምዘገዝገው ጀመር።ሁመራ በከባድ መሳሪያ ተኩስ ተናጠች።ግን በሁመራ ከተማ ላይ አንድ ንጹህ እንኳን አለመጎዳቱን አረጋግጫለሁ።አራጁ ቡድን ድንብርብሩ ወጣ።ሱሪይውን በእንትን ያበላሸም አለ ተብሏል።
አራጁ ቡድን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣የአማራ ልዩ ኃይል፣የአማራ ሚሊሻና ፋኖ ሁመራ የደረሰ መስሎት ነበር።በመሆኑም አራጁ ቡድን ቀድሞ በእጁ ያስገባቸውን አንቱ የተባሉትን የአማራ ተወላጅ ባለሃብቶ አቶ አማረ ጥሩነህን ጨምሮ ስምንት ንጹሃንን በመኪና ጭኖ ወደ እንድሪስ ፈረጠጠ።እነ አቶ አማረ ጥሩነህን እንድሪስ ላይ በግፍ አረዳቸው።ቢሆንም በወንድም የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት ቆራጥ ውሳኔ የንጹሃን ወገኖቻችን ነብስ ተረፈ።
አሁንም ወደ ኋላ ልመልሳችሁ።ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም መከላከያ ሰራዊቱ በተኛበት ሲጨፈጨፍ...ከጭፍጨፋ የተረፈው የሰራዊት አባላት ደፈጣ እየሰበረ የሸሸው ወደ ኤርትራ ግዛት ነው።የነበረው እንክብካቤ ሰምተናል።ማሰልቸት ስለሚሆንብኝ ከዚህ ላይ አልደገመውም።ግን ዛሬ ሻቢያ ጠላታችን ነው እያሉ ለሚያደነቁሩን የምለው አለኝ።ሻቢያ የዛሬ ጠላታችን ቢሆን ኑሮ የሻቢያ ወታደር አይደለም ቃታ ስቦ ከጭፍጨፋ ወደተረፈው ሰራዊት ተኩስ ከፍቶ ነውና... ደንበሩን እንኳን ጥርቅም አድርጎ ቢዘጋ ውጤቱን መገመት አያዳግትም።ይህ ሁኖ እያለ አንቱ የተባሉ የፖለቲካ ሊህቃኖቻችን ናቸው ያልናቸው ሳይቀሩ ዛሬ ሻቢያን ልክ እንደ ትህነግ ሰዎች በጠላትነት ሲከሱ ስንሰማ "ውሻ በበላበት ይጮሃል" የሚለውን አባባል ያስታውሰናል።
ይደገም ሱዳን ከግብጽ ጋር ሸርካና ጊዜ ጠብቃ ሉዐላዊነታችንን ስትዳፈር ከማናም አገራት ቀድሞ የተቃወመ ብቻ ሳይሆን ሱዳንንና ግብጽን ያስጠነቀቀ የኤርትራ መንግስት ነው።በከሰላ በኩል ወታደሩን ወደ ሱዳን ደንበር ያስጠጋ የኤርትራ መንግስት ነው።
እንደ መውጫ:-ታዲያ ዛሬ ሻቢያ እንዴት በአሁናዊ ጠላትነት ይከሰሳል? ጉምቱ ፖለቲከኞቹ ሳይቀር "በፖለቲካ መድረክ ዘላለማዊ ጠላትም ሆነ ዘላለማዊ ወዳጅ የለም" የሚለውን ሃቅ እንደምን ዘነጉት? እስቲ አሁን ከሻቢያ መንግስት በላይ ለእኛ የጠበቀ ወዳጅ ማን አለ?
ግልባጩ:- ለኤርትራን ፕሬስ
A mass grave prepared for the massacre of innocent Amharas in Humera town
By Amdemariam Ezra - Transcript: For the Eritrean Press
The image you see in the photo is of a well that was prepared for the massacre of innocent Amharas in Humera town. I saw this hole with my own eyes and left the image on my camera. However, the hole opened like this and it started with the Eritrean brotherhood under the Creator.
Not only did the TNG massacre the defense forces. On October 30, 2013, they massacred more than 1,200 Amharas in Maikadra (Kadra Water). The horrific massacre of Maikadra was to be repeated in Humera.
I have confirmed this during my visit to Humera. I spoke to a number of young survivors of the massacre. Mass grave Two of the members of the Defense Forces who were brutally shot in the town of Humera are buried. I have seen their graves.
So how did the catastrophic massacre like the Kadra River (Hidra River) end in Humera? Who saved more than 1,000 innocent Amharas from massacre?
Note that the Ethiopian Defense Forces, the Amhara Special Forces, the Amhara Militia, and the Fano Humera have not yet taken control. T-TPLF terrorists are rushing to take advantage of this gap. Victory has begun for the Tigrayan youths who are organized to kill the Amhara people. As we mourn the loss of the Kadra (Hadra River), our lives would have been doubled if Eritrean troops had not been on the border. Humera was bathed in innocent blood.
However, the Eritrean security forces heard that the unprovoked massacre was about to be repeated in Humera. The information came late. The massacre took place after the massacre. However, the Eritrean army arrived quickly to double the number of Hazans. They rescued more than 1,000 innocent souls. For the Eritrean security forces. They sent information to Eritrean government officials. The authorities did not waste a second. An Eritrean soldier began firing from the Eritrean territory to Humera. Humera was hit by heavy artillery fire. But I can confirm that not a single one was harmed in Humera town. The aging group broke the border.
The execution team thought that the Ethiopian Defense Forces, the Amhara Special Forces, the Amhara Militia and the Fano Humera had arrived. As a result, the executioner drove eight innocent people, including Antu Amhara investor Amare Tiruneh, to Andres. Nevertheless, the determination of our brother Eritrean Defense Forces saved the lives of our innocent people.
Let me take you back again. On October 24, 2013, when the defense forces were massacred ... The survivors of the massacre fled to Eritrea. We heard about his care. I am bored, so I did not repeat it. But today I have something to say to those who confuse us that Shabia is our enemy. "Shabia is our enemy today. He is not a Shabia soldier. He opened fire on the survivors of the massacre. Even if he closes the border, it is not hard to imagine the result. He cries out for help. ”
It is the Eritrean government that has not only opposed Sudan but also warned Sudan and Egypt when it violated Sudan's sovereignty over its alliance with Egypt. It is the Eritrean government that has sent troops to Sudan.
As a way out: So how can Shabia be accused of current hostility today? How did the Gumtu politicians forget the fact that "there is no eternal enemy or eternal friend in the political arena"? Who has a friend who is closer to us than the Shabia government?
Transcript: For the Eritrean Press
No comments:
Post a Comment