Shop Amazon

Friday, December 31, 2021

በካሊፎርኒያ የሚገኙ የዲያስፖራ ማህበረሰብ በአሸባሪው የጥፋት ቡድን ለወደሙ የጤና ተቋማትና ለመከላከያ ሰራዊት አገልግሎት የሚውሉ አምስት ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችና መድሀኒቶችን አስረክበዋል ።

በካሊፎርኒያ የሚገኙ የዲያስፖራ ማህበረሰብ በአሸባሪው የጥፋት ቡድን ለወደሙ የጤና ተቋማትና  ለመከላከያ ሰራዊት አገልግሎት የሚውሉ አምስት ሚሊዮን ብር  የሚያወጡ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችና መድሀኒቶችን አስረክበዋል  ። 
___________________
የአገር መከላከያ የውጭ ግንኙነት ዳይሬክተር  ብርጋዴል ጀነራል ቡልቲ ታደሰ በርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት ወራሪ እና የጥፋት ስብስብ የሆነው የሽብርተኛው የህውሀት ቡድን ገደብ በሌለው የስልጣን ፍላጎቱ እና  እኔ ካልኩት በቀር በሚል ስግብግብነት ሀገርን ከጀርባ ወግቶ ሰራዊት በትነናል ብሎ ካለህፍረት ነውሩን በአደባባይ ገልጿል። ይህም አልበቃ ብሎት በከፈተው ወረራ ከኢትዮጵያዊነት እሴት  ባፈነገጠ  ሁኔታ ህጻናትን፣ ባልቴቶችን እና አዛውንትን በግፍ ተግባር አዋርዷል ቤተ እምነት ደፍሯል። በዚህ ክፉ ጊዜ የዲያስፖራ ማህበረሰብም ህመማችንን ታማችሁ ጉዳታችንን ተጎድታችሁ ከጎናችን በመቆማችሁ የአገር መከላከያ ትልቅ ክብር አለው በማለት ለተደረገው የአምስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ  አመስግነዋል። 

የጤና ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ዶ/ር ተገኔ ረጋሳ በበኩላሸው  ባሸባሪው የህውሀት ቡድን በሰሜን ኢትዮጵያ በጤና ተቋማት ላይ ከፍተኛ ውድመትና ዘረፋ መፈጸማቸውን በዚህም ዜጎች ለከፋ የጤና ጉዳት መጋለጣቸውን ገልጸው  በጤና ተቋማቱ ላይ የደረሰውን የውድመት መጠን እና መልሶ ለማቋቋም ጤና ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በልዩ ትኩረት እየተሰራ ያለውን  ስራ  አስረድተዋል። 

በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እያደረጉ ያለው እርብርብ እጅግ የሚደነቅ መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር ተገኔ የጤና  ተቋማቱንም ቀድመው ከነበሩበት የተሻለ አገልግሎት የሚሰጡበትን ሁኔታ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት አሁንም ድጋፉ ተጠናክሮ  እንዲቀጥል ጥሪ አስተላልፈዋል።

 በቦሌ ኢንተርናሽናል አየር ማረፊያም የመድሀኒት እና የህክምና ግብአት መረከቢያ ዴስክ መዘጋጀቱን እና በዚህም ለጋሾች እንጋይጉላሉ ስርአት መበጀቱ ተገልጿል።

የካሊፎርኒያ አካባቢ ዲያስፖራ ማህበረሰብ ተወካይ አቶ  ነብዩ ኢሳያስ  በበኩላቸው እንደተናገሩት የህይወት ዋጋ እየከፈለ ሀገር እየታደገ ላለው መከላከያ ሰራዊት እና ይህንን  ጀግና ሰራዊት መርተው  ለታላቅ ድል ላበቁት እንዲሁም የኢትዮጵያውያንን አንገት ቀና ላደረጉና በያለንበት በኩራት እንድንራመድ ያስቻሉን  ታላቁ መሪያችን ዶ/ር አብይ አህመድ  ታላቅ አክብሮት እና ፍቅር  አለን ያሉ ሲሆን  የዲያስፖራው ማህነረሰብም ከሀገራችን ጎን ሆነን በሚያስፈልገን ድጋፍ ለማድረግ በድጋሚ ቃል እንገባለን  ሲሉ ተናግረዋል።


No comments:

Post a Comment