Shop Amazon

Sunday, January 2, 2022

በአገራችን ኢትዮጵያ በደረሰው ጦርነት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት በተደረገው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ በሳን ድያጎ ከተማ $195000 ዶላር ተሰበሰበ።




ሰበር ዜና

በአገራችን  ኢትዮጵያ  በደረሰው  ጦርነት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት በተደረገው  የገንዘብ  ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ  በሳን ድያጎ ከተማ  $195000 ዶላር መሰብሰቡ ተገለፀ።

       YebboMedia: (San Diego, CA) Jan 2, 2022 “ኢትዮጵያዊነት  ከዘር በላይ ነው” በሚል  መሪ ቃል  በጦርነት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቀሉ ወገኖችን  ለመርዳት  በሳንድያጎ ከተማ በተደረገው  የገንዘብ  ማሰባሰቢያ ዝግጅት  ላይ $195000 ዶላር  መዋጣቱን  የገንዝብ  አሰባሳቢው  ኮሚቴ ተወካይ የሆኑት  ወ/ሮ ቅድስት ብርሃኑ  አስታወቁ።  በሳንድያጎ  ከተማ  በሚገኘው  የኢትዮጵያ  ኮሚኒቲ  አስተባባሪነት  የተጀመረው  ይህ  ፕሮግራም  ላይ በከተማው  ውስጥ የሚገኙ የኢትያጵያዊያን  የሃይማኖት ተቋማት አባቶች፣ ኤርትራዊያን፣ ጥሪ  የተደረገላቸው  የአሜሪካ  ምክር  ቤት አባል እና እጅግ  በጣም ብዙ ቁጥር ያለው  የሳንድያጎ ከተማ  የሚኖሩ  ኢትዮጵያውያን  ተገኝተዋል።

የተዋጣው ገንዘብ  በሁለት ቦታ ተከፍሎ የሚሰጥ  ሲሆን  የመጀመሪያው  40%  የሚሆነው  ገንዘብ  EYZON  በሚባለው Online

የገቢ  ማሰባሰቢያ  ድረ ­_ገፅ ላይ  ገቢ  የሚደረግ  ሲሆን፣   ቀሪውን  60%  ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ  በባንክ  ቤት በኩል  ተልኮ ከኮሚቴው ሶስት  አባላት ያሉት  የተወካዮች  ቡድን  ወደ ኢትዮጵያ  የሚያቀና  ሲሆን  ከኢትዮጵያ  የእርዳታ  ቁሳቁሶችን  በመግዛት በወሎ እና  በአፋር ክልል  ለተጎዱ  ወገኖች  የሚያከፋፍል የሆናል። እገር መንገዳቸውንም  ወድ አገር ቤት ሲጓዙ በአገር ውስጥ  የተፈጠረውን  የመድሃኒት እና  የህክምና  ቁሳቁስ እጥረት ለመቅረፍ ከሳንድያጎ  ነዋሪ  ከሆኑ ከዶ/ር ታደሰ ደስታ  በእርዳታ የተገኙ  በህክምና ቁሳቁሶች የተሞሉ አራት ሻንጣዎችን  ይዘው  እንደሚሄዱ  ወ/ሮ  ቅድስት ገልፀዋል። 

በሌላ  በኩል ደግሞ  ኢትዮጵያን ለመርዳት የተያዘው  ታላቅ  ህሳቤ  ዘለቄታዊ  ለማድረግ እዚሁ  ሳንድያጎ  የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን   በየወሩ ከኪሳቸው   $100 ዶላር በወር እናዋጣ በሚል  መርህ   ማህበር  ተመስርቶ  እየተንቀሳቀሰ  ሲሆን፣ የህም ማህበር  በተለየ  መልኩ ተቋቁሞ  ገንዘቡ  ቀጥታ ወደ ኢትዮጵያ  እንዲገባ  መንግስት ባዘጋጀው  የባንክ  ሂሳብ  ውስጥ  ገቢ  የሚሆን ሲሆን፣ ማህበሩ በስድስት  ኢትዮጵያዊያን  ተጀምሮ  በመጀመሪው  ዙር $3600 አዋጥቶ  ቀጥታ  በተከፈተው  የመንግስት የባንክ  ሂሳብ  ያስገባ  ሲሆን፣  ይህንን የ$100 ማዋጣት  መርህ   ቢቻል  ከ ስድስት ወራት እስከ አንድ  አመት  ለማድረግ  የታሰበ  እቅድ  እንዳለ የዚህ  ማህበር  አስተባባሪ  ገልፅዋል። በእንግሊዘኛ  $100 challenge በሚለው መጠሪያ  ስም የሚጠራው ይህ  የገንዘብ  ማሰባሰቢ  ማህበር ሌሎች  ኢትዮጵያዊያንም  እንዲቀላቀሉ ጥሪውን  ያቀረበ ሲሆን፣  እንደ ማህበሩ  ተወካይ  የዚህ ማህበር አላማ  ኢትዮጵያ  የሚገጥሟትን ችግሮች  በአንዴ  ብቻ ሳይሆን  በቋሚነት ከግል ወጫችን  ላይ  $100 በወር  በመቆጠብ ለመርዳት የተዘጋጀ  የገንዘብ  ማሰባሰቢ  ዘዴ  እንደሆነ ተናግረዋል።  ይህን የተቀደሰ አላማ  ለመቀላቀል  የምትፈልጉ  ሰዎች  ኮሚቴው በሳንድያጎ  ከተማ  በሚገኙ  መደብሮች  እና  የንግድ  ተቋማት መረጃዎችን  እንደሚያገኙ  አስታውቀዋል።

 

የገንዝብ አሰባሰቢውን ኮሚቴ በመወክል  ወ/ሮ ቅድስት ብርሃኑ  እንዳሉት  ለዚህ ታላቅ  የአገር ጥሪ ምላሽ  የመስጠት  አላማ  ስኬታማነት ጊዜያቸውን  እና  ገንዘባቸውን  መሰዋት በማድረግ ሌት  ከቀን  የደከሙትን  የኮሚቴውን አባላት  እና   የሳንድያጎ ኢትዮጵያዊያንን እና ኤርትራዊያንን  እጅግ እናመግናለን  ብለዋል።

ሪፖርተር ፡ አምዴ ምትኩ 

 

 

 

 

 

 

No comments:

Post a Comment