እንደሚታወቀው በሰሜን ሸዋ የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በጦርነቱ ሙሉ በሙሉ ውድመት ደርሶበት ስራ ማቆሙ ይታወቃል።ይህን ተከትሎ የአጣዬ ሆስፒታልን ስራ ለማስጀመርና መልሶ ለማቋቋም የወራቤ ኮም/ስፔ/ሆስፒታል ሃላፊነት በመውሰድ የህክምና ቡድን በማደራጀት እንዲሁም ለድንገተኛ ፤ለእናቶችና ህጻናት አገልግሎት የሚያስፈልጉ የህክምና መሳሪያ, መድሃኒትና ሌሎች ዕቃዎችን በመያዝ ከሳምንት በፊት መንቀሳቀሳቸው ይታወቃል።ቡድኑ አጣዬ ሆስፒታል በመድረስ የያዙትን ግብዓት በማስረከብ ከአጣዬ ሆስፒታል ማኔጅመንት ጋር በመሆን ሁሉንም አገ/ት መስጫ ክፍሎችን በመዞር ችግሮችን በዝርዝር በመለየት የሙያና የስነልቦና ድጋፍ በማድረግ ታላቅ ሃላፊነት በመወጣት አገ/ት በማስጀመር ተመልሰዋል።ቡድኑ እንደተመለሱም ለሆስፒታሉ ማኔጅመንት የተለዩ ዝርዝር ጉዳዮችን በማቅረብ በአጭርና በረጅም ጊዜ የሚፈቱትን በመለየት አቅርቧል።በተለዩ ችግሮች መሰረት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን በመለየት ለሁለተኛ ዙር የተለያዩ የህክምና መሰሪያዎችን፤መድኃኒቶችን በመያዝ ወደ አጣዬ ሆስፒታል በመዉሰድ በአሁኑ ሰዓት የተመላላሽ፤ድንገተኛ ፤ተኝቶ ህክምና፤ላብራቶሪ ፤ፋርማሲ አገልግሎት መጀመሩን የአጣዬ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ አራጋው የገለፁ ሲሆን ለተደረገላቸው ድጋፍ እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን በመግለፅ የወራቤ ኮም/ስፔ/ሆስፒታል የማይተካ ወንድማማችነት ስላሳየን ከፍ ያለ ምስጋና አቅርቧል።ይህ ድጋፍ የአጣዬ ሆስፒታል ሙሉ አገልግሎት እስኪጀምር ድረስ የወራቤ ኮም/ስፔ/ሆስፒታል ድጋፉን እንደሚቀጥል የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ጀማል ሽፋ የገለፁ ሲሆን የህክምና ቡድኑ ላደረገው ድጋፍም ምስጋና አቅርቧል።
It is announced that the work of Attaye Hospital has begun
It is known that Attaye Primary Hospital in North Shoa was completely destroyed during the war. The team arrived at Ataye Hospital and handed over their resources to Ataye Hospital Management. Ato Aragaw, General Manager of Attaye Hospital, said that the outpatient, emergency, inpatient, laboratory and pharmaceutical service has just started. He thanked the hospital for its unwavering brotherhood.
No comments:
Post a Comment