Shop Amazon

Monday, January 10, 2022

"ኢትዮጵያዊነት ከዘር በላይ ነው" በሚል መሪ ቃል በሳንድያጎ ከተማ ለወገኖቻችን እርዳታ በተሰበሰብው ገንዘብ የእህል እርዳታ ይዞ የሄደው የልዑካን ቡድን ሰመራ ከተማ፣ አፋር ክልል ደረሰ።

"ኢትዮጵያዊነት ከዘር በላይ ነው" በሚል መሪ ቃል  በሳንድያጎ ከተማ ለወገኖቻችን እርዳታ  በተሰበሰብው ገንዘብ የእህል  እርዳታ ይዞ የሄደው  የልዑካን ቡድን  ሰመራ ከተማ አፋር ክልል ደረሰ።

የልኡካን ቡድኑ አባላት ወ/ሮ ቅድስት ብርሃኑ፣ አቶ አቶ ስዮም ደገፋ እና ወ/ሮ እመቤት እንግዳው 

(YebboMedia Jan 10,2022 ጥር ፪፣2ሺ፲፬) "ኢትዮጵያዊነት ከዘር በላይ ነው" በሚል መሪ ቃል  በሳንድያጎ ከተማ ለወገኖቻችን እርዳታ  እንዲደርስ ከተደረገው  የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት  ላይ ከተዋጣው $195000 ዶላር ላይ 60% የሚሆነው  በባንክ ቤት ቀጥታ ወደ ኢትዮጵያ በማስተላለፍ ኢትዮጵያ ሄዶ ከአገር ውስጥ የእርዳታ እህል  በመግዛት ወደ አፋር ክልል ያቀናው የልዑኳን ቡድን ሳመራ  ከተማ በመደረስ እርዳታውን ነገ  እንደሚያከፋፍል  ገለፀ። 40% የሚሆነው  በእርዳታ  የተሰበሰብ  ገንዘብ በ eyezonethiopia.com ላይ በተሰራው  የእርዳታ  ማሰሳበስቢያ ድረ ገፅ ላይ ገቢ መሆኑን  ባለፈው  ባጠናቀርነው ሪፖርት ላይ ተዘግቧል።  

የልዑካኑ  ቡድን  አስተባባሪ  የሆኑት  ወ/ሮ ቅድስት ብርሃኑ  በውስጥ  መስመር  እንደገለፁት  ዛሬ  ማምሻውን ሰመራ  ከተማ  የገቡ  ሲሆን  በነገው  እለት ለ800 አባወራዎች  የሚሆን 200 ኩንታል  የበቆሎ  ዱቄት፣ 80 ኩንታል ሩዝ፣ 2400 ሊትር ዘይት  የሚለግሱ ሲሆን ከዚህም  በተጨማሪ  ለ200 ቤተሰቦች 5 ፍይሎችን የሚያበረክቱ  መሆኑን  ገልፀውልናል።
  
በልዑካኑ ቡድን እቅድ መሰረት እረዳታውን በወሎ እና በአፋር ለተጎዱ ወገኖች ማከፋፈል ስለሆነ ሌላ  ተጨማሪ  መረጃ  ስናገኝ  ለንባብ  እናበቀዋለን።. 



                                            
ሪፖርተር፤ ዐም

No comments:

Post a Comment