Shop Amazon

Tuesday, January 4, 2022

ዳያስፖራው የተሳተፈበት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር እየተካሄደ ነው

ዳያስፖራው የተሳተፈበት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር እየተካሄደ ነው
******************

የዳያስፖራውን ማህብረሰብ ያሳተፈ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው። 

መርሀ ግብሩ በአዲስ አበባ ከተማ በተዘጋጀው የዳያስፖራ ፓርክ ውስጥ እየተካሄደ ሲሆን በከንቲባ አዳነች አበቤ መሪነት በርካታ የዳያስፖራ አባላት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ እያካሄዱ ይገኛሉ።

ከንቲባዋ በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክትም፤  በውጭው ዓለም ኢትዮጵያ ጫና ሲደርስባት ዳያስፖራው አቅሙን ሳይሰስት ትግል ሲያደርግ መቆየቱን ጠቅሰዋል።

ትውልድ እንዲማርና ወቅቱን እንዲያስብ እንዲሁም አካባቢን ለማልማት ለዳያስፖራው መታሠቢያ ይሆን ዘንድ ከተማ አስተዳደሩ የዳያስፖራ ፓርክ ማዘጋጀቱን ተናግረዋል። 

ይህ መታሠቢያ ትርጉሙ ከአረንጓዴ ልማት በላይ ነው። የዳያስፖራው የአረንጓዴ አሻራ ተሳትፎም እንደሚበረታታ እንደሆነ ገልጸዋል።

በመርሀ ግብሩ ተሳትፎ ያደረጉ ዳያስፖራዎች የእናት አገር ጥሪን ተቀብለው አሻራ ለማኖር መብቃታቸው ልዩ ስሜት እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል። 

በቀጣይም መሰል ተሳትፎዎችን በማጉላት አገርን በሁሉም መስክ ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል ሲል ኢ ፕ ድ ዘግቧል።
A green fingerprint program is underway with the participation of the Diaspora
 ******************

 A green fingerprint transplanting program involving the Diaspora community is underway in Addis Ababa.

 The program is being held at the Diaspora Park in Addis Ababa.

 In a message delivered by the mayor at the opening of the program:  He said the Diaspora has been struggling despite Ethiopia's pressure from the outside world.

 He said the city administration has set up a Diaspora Park as a reminder to the Diaspora to educate the generation and think about the season and to develop the environment.

 This memorial means more than green development.  He said the participation of the Diaspora in the green footprint is also encouraged.

 The Diaspora who participated in the program expressed their special feeling that they were able to accept the call of the motherland and leave their mark.

 He further said that they are ready to support the country in all fields by highlighting such participation.



No comments:

Post a Comment