Keria Ibrahim responds to Prison complaint
(YouTube daily updates)
The Federal High Court's Lideta Division I Anti-Terrorism and Constitutional Affairs Criminal Trial was scheduled for today to respond to the complaints filed by the 6 defendants. The 8th defendant, Keria Ibrahim, and the 19th defendant, Dr. Solomon Kidane, did not appear in court today due to illness.
The administration of the prison responded to a written complaint by former speaker of the House of Federation, Keria Ibrahim, stating that he was not allowed to speak on the phone in Tigrinya.
In addition, they responded to a complaint alleging that they were denied access to a notebook.
Defendants' lawyer Wendesen Bekele, who appeared in court today, argued that the ban was unconstitutional and illegal.
It is learned that the court has rescheduled the hearing for January 17 and will issue an order to investigate the case only.
Source: Fresh - New Morning
ኬሪያ ኢብራሒም ባቀረቡት አቤቱታ ጉዳይ ዛሬ ማረሚያ ቤት ምላሽ ሰጠ
(የኢትዩትዩብ እለታዊ መረጃዎች )
በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብርና የህገመንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ለዛሬ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር በ6 ተከሳሾች በተነሱ አቤቱታዎች ላይ መልስ እንዲሰጥ በያዘው ቀጠሮ ችሎቱ የተሰየመ ሲሆን፤ በዛሬው ቀጠሮ 8ኛ ተከሳሽ ኬሪያ ኢብራሂም እና 19 ኛ ተከሳሽ ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ በህመም ምክንያት በችሎት አልቀረቡም ፡፡
የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር የቀድሞ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዬ የነበሩት ኬሪያ ኢብራሂም በትግረኛ ቋንቋ ስልክ ለማውራት ስለተከለከልን እንዲፈቀድልት ይታዘዝልን ስሉ ያቀረቡትን አቤቱታን በተመለከተ ማረሚያ ቤቱ በስልክ ማውራትም የተከለከለው ለአገሪቷ ደህንነት ክትትል ስለሚደረግ መሆኑን በጽሁፍ ምላሽ ሰቷል።
በተጨማሪም በማስታወሻ ደብተር ተከልክለናል ሲሉ ባቀረቡት አቤቱታ ላይም ማረሚያ ቤቱ ከፍርድ ቤት ማህተም ካለበት ሰነድ ውጪ መያዝ የተከለከለው በደህንንነት መከታተያ ስርዓት መሰረት መሆኑን ምላሽ ሰቷል።
ዛሬ በችሎት የተገኘው የተከሳሾች ጠበቃ ወንደሰን በቀለ ኬሪያ ኢብራሂም በስልክ በትግረኛ ቋንቋ ማውራት ህገመንግስታዊ መብታቸው መሆኑን በማብራራት ክልከላው ሰብዓዊ መብታቸውን የሚጋፋ እና ህግን የተከተለ አደለም ሲል መቃወሚያ አሰምቷል።
ፍርድ ቤቱም አቤቱታ በቀረበባቸው ጉዳዮች ብቻ መርምሮ ትዛዝ ለመስጠት ለጥር 17 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱም ታውቋል።
ምንጭ፡- አዲስ ማለዳ
No comments:
Post a Comment