Shop Amazon

Tuesday, January 4, 2022

Large quantities of wheat and oil were purchased to stabilize market prices

የገበያ ዋጋ ለማረጋጋት ከፍተኛ መጠን ያለው የስንዴና ዘይት ግዢ ተፈጸመ
******************
የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ከማስፍን አንጻር የዋጋ ግሽበትን የመቆጣጠርና የገበያ ዋጋን የማረጋጋት ፋይዳ ያለው የ4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴና የ12.5 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ግዢ መፈጸሙን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት የመቶ ቀን እቅድ አፈጻጸም ግምገማ በተካሄደበት ወቅት እንደተገለጸው ባለፉት ጥቅምትና ህዳር ወራት የ4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ግዥ  ተፈፅሟል፡፡  

ግዥ ከተፈፀመው ስንዴ ውስጥ አንድ ሚሊዮን ሀምሳ አንድ ሺ አንድ መቶ ስልሳ ኩንታል ስንዴ ወደ ሃገር ውስጥ የገባ ሲሆን ይህም የስንዴ ዋጋ ከፍ እንዳይል የራሱ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ነው የተገለጸው፡፡ 

ቀሪው ስንዴ በተቻለ ፍጥነት ተጓጉዞ ወደ ሀገር ውስጥ አንደሚገባም ታወቋል፡፡
በዚሁ ወቅት የ12.5 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ግዢ ተፈጽሞ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት በሂደት ላይ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

የምግብ ዘይትና ዱቄት ከውጭ በፍራንኮ ቫሉታ (አስመጪዎች በራሳቸው የውጭ ምንዛሪ) እንዲያስገቡ በመደረጉ የሸቀጦች ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል ማስቻሉም ተገልጽዋል፡፡

በጥቅምት ወር 2014 ዓ.ም 34.2 በመቶ የነበረ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በህዳር ወር ወደ 33.0 በመቶ ዝቅ ብሏል ተብሏል። 

የሕዳር 2014 ወርሃዊ የምግብ ዋጋ ግሽበት ካለፈው ጥቅምት 2014 ጋር ሲነጻጸር በ1.8 በመቶ የቀነሰ ሲሆን በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት 1.0 ከመቶ የጨመረ መሆኑን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው  መረጃው  ያመለክታል፡፡
Large quantities of wheat and oil were purchased to stabilize market prices
 ******************
 The Ministry of Finance said it has procured 4 million quintals of wheat and 12.5 million liters of cooking oil, which is important for controlling inflation and stabilizing market prices.

 According to the Ministry of Finance and its affiliated institutions, 4 million quintals of wheat was procured last October and November.

 Out of the purchased wheat, one million fifty-one thousand one hundred and sixty quintals of wheat was imported, which is said to contribute to the increase in the price of wheat.

 It is learned that the rest of the wheat will be transported as soon as possible.
 Meanwhile, 12.5 million liters of cooking oil has been procured and is in the process of being imported.

 It is also stated that the importation of cooking oil and flour by Franco Valuta (importers on their own foreign exchange) has helped keep commodity prices stable.

 Total inflation fell to 34.0 percent in November 2014 from 34.2 percent in November 2014.

 According to the Ministry of Finance, inflation in non-food items increased by 1.0 percent in November 2014, while food inflation fell by 1.8 percent compared to October 2014.

No comments:

Post a Comment