Shop Amazon

Thursday, September 15, 2022

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአሰልጣኝ ውበቱ አባተን ውል አራዘመ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአሰልጣኝ ውበቱ አባተን ውል አራዘመ
****************************

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ውላቸውን ለማራዘም ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በዛሬው ዕለት ስምምነት ፈፅመዋል።

በ2013 ዓ.ም ብሔራዊ ቡድናችንን በመረከብ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በስራ ላይ የቆዩት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በቆይታቸው ብሔራዊ ቡድኑን ወደ አፍሪካ ዋንጫ ከስምንት ዓመት በኋላ የተመለሰ ሲሆን በቅርቡ ደግሞ በአልጄርያ ለሚከናወነው የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) ከስድስት ዓመት ቆይታ በኋላ የውድድር ተሳትፎ አሳክቷል። 

አሰልጣኙ ውላቸው መጠናቀቁን ተከትሎም ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት (እስከ መስከረም 2017) በዋና አሰልጣኝነት እንዲቀጥሉ በዛሬው ዕለት የውል ስምምነት ተፈራርመዋል።

ከውል ማራዘም ጋር የተያያዙ ዝርዝሮች እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለቻን ውድድር ማለፉን የተመለከተ ማብራርያ መስከረም 9 ቀን 2015 ዓ.ም ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጥ መሆኑን ከፌዴሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

Ethiopian Football Federation has extended the contract of coach Ubutu Abate
 ******************************

 The head coach of the Ethiopian national team, Ubutu Abate, has signed an agreement with the Ethiopian Football Federation today to extend his contract.

 After taking over our national team in 2013, the coach who has been on the job for the past two years, Ubutu Abate, returned the national team to the Africa Cup of Nations after eight years of his stay, and recently he has achieved participation in the African Nations Championship (CHAN) held in Algeria after a six-year absence.

 The coach signed a contract today to continue as head coach for the next two years (until September 2017) following the completion of his contract.

 Information from the federation indicates that the details related to the extension of the contract and the explanation regarding the passing of the Ethiopian national team to the Chan competition will be given on September 9, 2015.

No comments:

Post a Comment