Shop Amazon
Monday, July 17, 2023
የቄራ ሰራተኛዋ
ከለታት አንድ ቀን አንድ የስጋ ማከፋፈያ ፋብሪካ (ቄራ) ውስጥ የምሰራ ሴት ነበረች።አንድ ቀን ስራዋን ከመጨረሷ በፊት ወደ ስጋ ማቀዝቃዛ ክፍል (ፍሪዘር) የሆነ ነገር ለመመርመር እንደገባች የማቀዝቀዣው በር በራሷ ውስጥ እንዳለች በላይላይ ይዘጋል፣ ሴትዮዋ እርዱኝ ብላ ብትጮህ ማንም ሊሰማት አልቻለም። አብዛኞቹ ሠራተኞችም ወደቤታቸው ሄደዋል። በቆፈን እና በብርድ ስትቆራመድ አምስት አአታት አለፉ። በመጨረሻም ጣረ ሞት ሲያንዛብባት በሩ ሳይታሰብ ተከፈተና ሴትዮዋ ከመሞት በተአምር ዳነች። በሩን የከፈተው የቄራው የጥበቃ ሰራተኛ ነበር። ከዚያም ነፍሷ መለስ ሲል እጅግ ካመሰሰገነችው በኋላ የጥበቃ ሰራተኛውን እንዴት እንደመጣ እና እንዴት በሩን እንደከፈተላት ትጠይቀዋለ የእሱ ማብራሪያ፡- “በዚህ ቄራ ለ35 ዓመታት ሰርቻለሁ። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞች በየቀኑ ይግባሉ ይውጣሉ ፣ ግን እርስዎ እና ከጥቂቶች በስተቀር ሰው መሆኔን እንኳ የሚያስታውስ የለም። እርስዎ በጠዋት ሰላምታ የሚሰጡኝ እና ሁልጊዜ ስራ ጨርስው ሲሄዱ ሲሄዱ ደህና እደር ብለውኝ የሚሄዱ ጥሩ ሰው ነዎት፣ ዛሬ ግን ያንን የለመድሁትን ደህና እደር ሰላምታ እና ያንተን 'ሃይ' እና 'ባይ' በጉጉት እተጠባበቅሁ ሳላገኝ ስቀር ልቤ ተረበሸ፣ ለራሴም እንዲህ ብዬ ነገርሁት " ይች ሴት የሆነ ችግር ተፈጥሮ ነው እንጂ ሳትመጣ አትቀርም ብየ፣ እና ፈልግ" ብየ ለራሴ ትዛዝ ሰጠሁ፣ ግቢውን ሁሉ ዞርሁ፣ ፍለጋውን የጀመርሁ ከአምስት ሰዓታት በፊት ነው፣ ተስፋ ሳልቆርጥ ስፈትሽ አሁን አገኘሆት፣ ልቤንም ደስ ብሎኛል፣ ብድሬንም መልሻለሁ" ብሎ ይነግራታል። እርስዎም ትሑት ሲሆኑ, ሲዎዱ እና እና በዙሪያው ያሉትን ሲያከብሩ ያ ጥሩ ስራ አንድ ቀን በሌላ መንገድ ለርስዎም ይመጣል
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment