የቦ ኮሚኒኬሽ ኔት ዎርክ በእናንተው ለእናንተው የተሰመሰረተ ድርጀት ። ከ 25 አመት በላይ የስራ ልምድ።
የቦ ኮሚኒኬሽን ኔት ዎርክ እንደ አሁኑ ኢንተርኔር በሽ በሽ ሳይሆን ገና ጥንት ብዙሃኑ ኢንተርኔርን ለቅንጦት ብቻ በሚመስልበት ጊዜ የህዝቡ አስተሳስብ በሂደት ይቀየራል በሚል አስተሳሰብ ኢትዮጵያን ከሌሎች አገሮች ወደ ኋላ እንዳትቀር እና ከዛሬው ቲክኖሎጂ ጋር አብራ እንድትራመድ ይረዳል በሚል ታስቦ የተመሰረት ድርጅት ነው።
የቦ ሲመሰረት ይህ አሁን የምታዮት ሁሉ አገልግሎት እንሰጣለን ብለን አልነበረም። በወቅትቱ ስለ ኢትዮጵያ የሚገልፁ ድረ ገፆች ያሉት ወይ በውጭ አገር ሰዎች የሚፃፉ መፃፅፍት፣ ቪዲዮዎች፣ ፎቶ ግራፎች እና የድምፅ ቅጅዎች ብቻ በበዙበት፣ ነገር ግን ለኢትዮጵያ ተብሎ የተመሰረተ በኢትዮጵያዊያን የሚዘጋጅ ብዙ ድረ ገፆ ባልነበረበት ጊዜ ነው። በዚያ ወቅት ነው የቦ የኢትዮጵያን ባህል፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት፣ የታሪክ ፣ የኢትዮጵያ እንቁ ልጆቿን እና ሌሎችንም የኢትዮጵያ ትሩፋት ለአለም ህዝብ ለማስተዋወቅ www.yebbo.com የሚለውን ድረ ገፅ ይዘን ብቅ ያልነው።
እኛ ስንጀምር አንድም የኢትዮጵያ መንግስት ኢምባሲ፣ ሚኒስቴርም ሆነ ባለ ስልጣን ድረ ገፅ አልነበረም ፣ አየር መንገድም ሆነ የኢትዮጵያ ምግብ ቤቶች፣ ሱቆች ፣ ዩኒቨርስቲዎች እና የትምህርት ተቋማት ምንም አይነት የኢንተርኔት ድረ ገፅ አልነበራቸው።
ታዲያ የኔው ነው የቦ ኮሙኒኬሽን ኔትዎርክ ሙሉ ኋይሉን ለኢትዮጵያ ብቻ አድርጎ የተመሰረተ ኩባያ እንዲሆን ያደረገው። የቦ የተመሰረተው ሳይማር ያስተማርውን ሳይኖራት በነፃ ያስተማረችን አገር ብድር ለመክፈል ታስቦ የተሰራ ነው። ያኔ ገንዘብ ማግኘት አላማም እቅድም አልነበረም።እስከ 2002 ድረስ የቦ የነፃ አገልግሎት ነበር። ግን ታሪክን እና አመጣጥን ብዙዎች ሳያውቁ ይቀሩና ወይም እኛ የደከምንበትን እና የለፋንበት ሃሳብ ይሰርቁና የራሳቸው አስመስለው ፈጣሪ እና ፈላጭ ቆራጭ መስለው የሚታዩት ። ብዙዎች በሚኖራቸው የፖለቲካ እና የዘር መተሳሰር አንዳንዴ በውሸት ያገኙትን ስራ የሚያንፀባርቅላቸው አይጠፋም ይባስ ብለው በቴሌቭዥን እና በሚዲያ ፈጣሪ መስለው ያወራሉ። ታዲያ የቦ የፈጠራቸው ብዙ የመጀመሪያ ስራዎች ውስጥ ጥቂቶቹ።
1ኛ የአማርኛ የመጀመሪያውን ኪቦድ መፃፊያ
2ኛ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን በኢንተርኔት ላይ የጉዞ ትኬት መቁረጫ
3ኛ የመጀመሪያውን የኢትዮጵያ የአትሌቶች ድረ ገፅ
4ኛ የመጀመሪያውን የኢትዮጵያ የንግድ ማውጫ
5ኛ የመጀመሪያውን የኢትዮጵያ አመታዊ የሙዚቃ ሽልማት
6ኛ የመጀመርያውን የኢትዮጵያ በአሜሪካ የኢትዮጵያ የሬስቶራንቶች ማውጫ
7ኛ የመጀመሪያውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ የቤተ ክርስትያኖች ማውጫ
8ኛ የመጀመሪያው የኖኪያ ቲሌፎን ወደ አማርኛ መቀየር ፕሮጄክ ተሳታፊ
9ኛ የመጀመሪያ በኢንተርኔት ላይ የኢትዮጵያ የውክልና ስልጣን መስሪያ ወብ ሳይት
10ኛ የመጀመሪያ የአፍሪካ ቋንቋ ትርጉም እና ሶፍትዌር ኩባንያ
እነዚህ ከብዙ በጥቂቱ ናቸው።
ታዲያ ጊዜ በሄደ እና ቲክኖሎጂ በተሻሻለ ቁጥር ነገሮች እየቀለሉ እና እየረከሱ ይመጣሉ። ለምሳሌ የዛሬ 25 አመት አንድ ፎቶ ወደ ኢንተርኔት ለማስገባት በጣም ብዙ ጣጣ ነበረው። ሆኖም የቴክኖሎጂ መራቀቅ እና አዳዲስ ፈጠራዎች መምጣት ዛሬ ቪዲዮ ኢንተርኔት ላይ መጫን ብቻ ሳይሆን ቪዲዮ እየተያዩ ማውራት የእለት ከእለት ስራችን ሆኗል። በዚህ አጋጣሚ የቦን የመጀመሪያው በቴሌፎን ዋይርለስ ኔት ዎርክ (Wirless Video Streaming ) ተጠቅሞ በቴሌፎን ቪዲዮን የመላክ ፕሮጄክት ላይ ከሌላ ኩባያ ተቀጣሪ በመሆን የየቦ ኖሚኒኬሽ ኔት ወርክ መስራች ኢንጂነር የዚያ ቲክኖሎጂ መስራቾ የመጀመሪያ ሰዎች ውስጥ አንዱ ነው።
ታዲያ የቦ ዛሬ የት ነው?
የቦ አገልግሎቱን እያሰፋ እና እያጠናከረ ከ25 አመት በፊት የተነሳበትን ዋና ራይ ሳይተው ወደ ፊት እየገሰገሰ እና ከቴክኖሎጂ ጋር እየተራመደ ይገኛል። ዛሬ የቦ ከ75 አይነት በላይ አገልግሎቶችን ለአለም አቀፍ ደንበኞቹ እየሰጠ ይገኛል። በአጠቃላይ በየቦ የሚሰጡ አገልግሎቶች መዘርዘሩ ደንበኞቻችን ሊያደናግር ስለሚችል ሁሉንም በአምስት ምድቦች አጠቃለናቸዋል።
1ኛ ኢንጅነሪን እና ዲዛይን (Yebbo.com)፡ በዚህ ምድብ በየቦ ኮሙኒኬሽን አመካኝነት የሶፍትዌር ዲዛይን፣ የወብ ሳት ዲዛይን እና የኢንጂነሪን ምክር እና አገልግሎት እንሰጣለን።
2ኛ ቋንቋ እና ሎካላዜሽን (Ethiotrans.com) ፡ በዚህ ምድብ ከ150 በላይ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ከ 4500 በላይ የቋንቋ ባለሙያዎችን ያለን ሲሆን በዚህ ምድብ የፅሁፍ ትርጉም ስራ (translation) ፣ በቃል ትርጉም ስራ (interpretation) የሶፍት ዌር ትርጉም ስራ (localization and globalization) ፣ የፊልም እና የቪዲዮ ትርጉም (Subtitling and Voiceover) ስራ እና የመሳሰሉትን አገልግሎቶች እንሰጣለን።
3ኛ የጉዞ ወኪል (YebboTravel)፡ በዚህ ምድብ በአለም ላይ ካሉ ከ 700 በላይ የአየር መንገዶችን የሚያጠቃልል የአየር፣ የሆቴል ምዝገባ እና የመኪና መከራየት አገልግሎት እንሰጣለን። አንዲሁም የፓስፖርት፣ የቪዛ፣ የቢጫ ካር ፣ የውክልና ሰነድ አገልግሎት እንሰጣለን።
4ኛ ታክስ (YebboTax)፡ በዚህ ምድብ በአሜሪካ መንግስት ልዩ ፈቃድ አግኝተን የግለሰቦችን እና የድርጅቶን አመታዊ ገቢ ታክስ እንሰራለን ።
5ኛ የህትመት እና ማታዎቂያ (YebboMedia)፡ በዚህ ምድብ የማስታዎቅያ እና የንግድ ወይም የድርጀት መገልገያ የሚሆኑ ህትመቶችን (imprints) እናዘጋጃልን፣ እንዲሁም ማስታዎቂያዎችን እና ቪዲዮዎችን እናዘጋጃለን ።
በተቻለን መጠን የምንሰጣቸውን አገልግሎቶች በነዚህ ምድቦች እናስቀምጥ እንጂ ለምሳሌ የጣት አሻራ (finger printing service) ፣ የፓስፖርት እና ቪዛ ፎቶ (global passport and visa service) ፣ የአቃ መላክ አገልግሎት (Global Shipping) ፣ የህክምና ኢንሹራንስ አገልግሎት (Health Insurance enrolment service) ፣ አንሰጣለን ።
ለዚህም ነው ስማችንን One Stop Global Business Center ያልነው። አላማችን ደንበኞቻችን ከእኛ ቢሮ ከመጡ ጊዚያቸውን እና ገንዘባቸውን ቆጥበው በአንድ ቦታ ሁሉንም አገልግሎት እንዲያገኙ ነው።
በበለጠ ስለምንሰታቸው አገልግሎቶች እና ምክሮች ለመረዳት እባክዎ የድረ ገፃችንን www.yebbo.com ይጎብኙ ወይም በስልክ ቁጥር 619 255 5530 ይደውሉልን ።
No comments:
Post a Comment