ግብፅ የግድቡን ሙሌት ለማስቆም ያላት የመጨረሻ እድል..?
ግብፃዊው ምሁር የጠቆሙት ዒላማ
የዓባይ:ልጅ
የአለም አቀፍ ውሃዎች እና የግድብ ኤክስፐርት የሆኑት ግብፃዊ ምሁር ዶ/ር መሀመድ ሃፌዝ፣ በህዳሴ ግድቡ ቀሪ የውሃ ሙሌት እንዳይደረግበት ያደናቅፋል ያሉትንና ለግብፅ የመጨረሻው እድል ነው ሲሉ የሰጡትን ሐሳብ እንደ "አረብ-21 ቴሌቪዥን ያሉ ሚዲያዎች እያሰራጩት ይገኛል።
ከ “አረብ 21” ጋር በነበራቸው ቆይታ “ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር ችግሩን ለመፍታት ለ12 ዓመታት የተደረጉ ድርድሮችና ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ያለስኬት መቋጨታቸውን ተከትሎ የትኛውም አማራጮች አልቀዋል" ያሉ ሲሆን ጉዳዩን "በተመድ. የፀጥታው ምክር ቤት፣ በአፍሪካ ህብረት፣ በአረብ ሊግ፣ በአውሮፓ ህብረት፤ እንዲሁም በዩናይትድ ስቴትስ በኩል አዲስ አበባ ላይ ግፊት እንዲያደርጉ የተደረጉ ሙከራዎች ኢትዮጵያን ማሳመን አልቻሉም።"
ሃፌዝ አክለውም “ካይሮ ከአዲስ አበባ ጋር በቅርቡ የተደረገውን ድርድር መቀበሏ ስህተት ነበር። ኢትዮጵያ በወቅቱ የግድቡን ቀጣይ ስራ ለማከናወንና እና የግድቡን የውሃ ሙሌት ለማከናወን ምቹ አጋጣሚ ያገኘችበት ነው። በዚህም ውሃውን ከኤሌክትሪክ ማምረት ባለፈ ለሌሎች ልማቶችም ወደ መጠቀም ተሸጋግራለች።"
ከዚህ በተያያዘ የግብፁ የመስኖ ሚኒስትር ሃኒ ስወይለም ባለፈው ሳምንት የህዳሴውን ግድብ በተመለከተ አዲስ ለውጥ አለመኖሩንና ወደ ድርድር እንደማይመለሱም የገለፁበትንና፤ ከዚህ ይልቅ የግብፅ መንግስት ግድቡ ችግር በሚከስትበት ወቅት አስፈላጊውን የሃይል እርምጃ የመውሰድ መብት አለው" ማለታቸውን አስመልክተውም ፕሮፌሰሩ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ይኸውም የግድቡ አካል በሆነ አንድ ክፍል ላይ ወታደራዊ ጥቃት ኢላማውን ጠብቆ ሊካሄድ ይገባዋል የሚል ነው።
"አል-ሙፊድ" ላይ ወታደራዊ ጥቃት የመጨረሻው ዕድል ነው
ሃፌዝ እንዳሉት፣ “አሁን ላይ በህዳሴ ግድቡ ላይም ሆነ በኮርቻ ግድቡ Saddle Dam ላይ ወታደራዊ ድብደባ ለማድረግ የማይቻልበት ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው። ግድቡ ከ 41 ቢሊዮን ሜትሪክ ኪዩብ ውሃ የያዘ መሆኑ በግብፅም ሆነ ሱዳን ላይ ከፍተኛ ጥፋትና ውድመት የሚያስከትል ይሆናል።
በሁሉም ሀገራት ላይ ምንም ጉዳት የማያስከትለው የጥቃት ኢላማ ነው በማለት ሲናገሩ ግብፃዊው ፕሮፌሰር በዚህኛው ጥቃት ሶስቱም ሀገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ ግብፅ እና ሱዳን ላይ ጉዳት የማያስከትል" በማለትም አስገራም ሀተታ ተጠቅመዋል።
ፕሮፌሰሩ አሁናዊው ኢላማ ነው ያሉት የግድቡ ክፍል የውሃ ማስተንፈሻው Spill Way ሲሆን፤ በአምስተኛው የግድቡ የውሃ ሙሌት ላይ የማከማቻ ሀይቁ ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ 640 ሜትር ገደማ ይደርሳል ካሉ በኋላ፤ የግድቡ ማስተንፈሻ Spill Way ላይ ኢላማውን የጠበቀ ጥቃት ማድረስ “ማንም ላይ ጉዳት አያደርስም። ሁሉንም(ሶስቱንም ሀገራት) አሸናፊ ያደርጋል። ይህም ማለት ኢትዮጵያ 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የማጠራቀም ጉዞዋ ይገታል። የግድቡ ሃይቅ ከፍታም የ 640 ሜትር ኢላማውን እንዳያሳካ ያደርጋል። ይልቁንም ኢትዮጵያ ከዚህ በሚተርፋት ውሃ ኤሌክትሪኳን ብቻ ያለ ችግር እያመነጨት ብቻ የምትጠቀም ትሆናለች" ብለዋል። _____||
እንደሚታወቀው የህዳሴ ግድቡ የውሃ ማስተንፈሻ (Spillway)፤ በተለይም "main controlled spillway" የሚባለው ክፍል በግድቡ የ 624.9 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ግድቡ በ 630 እና 640 ሜትር የውሃ ከፍታው ላይ በሚኖረው የሃይል ማመንጨት ተግባር ውስጥ ግልጋሎት ይሰጣል። የድንገተኛ ማስተንፈሻው emergency spillway በግድቡ 642 ሜትር ላይ ሲገኝ open spillway ደግሞ 640 ላይ ነው የሚገኘው።
ግብፃዊ ልሂቃን ቀደም ባሉት አመታት የጥቃት ኢላማ ይሆን ዘንድ ሲጠቅሱት የነበረው የህዳሴ ግድቡ ከፍል የኮርቻ ግድቡ Saddle Dam እንደነበር አይዘነጋም። ይኸው የኮርቻ ግድብ የህዳሴ ግድቡ ከ 90 ሜትር ወይም (590 amsl) በላይ ከፍታ በመጨመር የግድቡ ከፍታ ወደ 145 ሜትር(645 amsl) ማሳደግ የቻለ ነው። ይህም ከግድቡ የማመንጨት አቅም ውስጥ ከ 1 ሺህ 400 ሜጋዋት በላይ ያለውን ጭማሪ ሁሉ ማምጣት የቻለ፤ እንዲሁም የግድቡን የውሃ ክምችት ከ 11 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ በላይ በማድረግ ይሆን ነበር ይላሉ ወደ 74 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ከፍ ማድረግ ያስቻለ ነው - የህዳሴው Saddle Dam የኮርቻ ግድብ ..!
No comments:
Post a Comment