Under what circumstances can a landowner’s map( title ) be cancelled?Ethiopian Law
1. The land ownership certificate issued by the land administration bodies of urban administrations is the best indication of the owner’s right to that piece of land!
According to Article 1195 of the Civil Code, a person who holds a map is presumed to be the legal owner of the land.
However, this presumption of ownership, which is taken by law, can be challenged in the circumstances set out in the law!
2. When we come to the question of whether a landowner can appeal against the land ownership certificate issued by the relevant land administration body. The answer is yes.
3. What are the reasons for an land ownership certificate being revoked?
It can be understood from Articles 1196 & 1197 of the Civil Code that an administrative body that has issued a land ownership certificate can revoke the map!
However, a person who has been issued a map claiming to be the owner of a piece of land can be held liable for the map being issued if there is a situation where the map was created before it was issued and the owner of the map obtained the proof of ownership without due process.
In other words, the party who cancels the map has the burden of proving that the map was issued without due process!
4. The Court of Appeal has given various mandatory interpretations of the cancellation of a map.
Among these, the ones given in M/No. 42501 and M/No. 99071 are mentioned.
In these cases, the Federal Supreme Court has clarified 3 basic limitations on the power of land administrations and city administrations to cancel maps!
4.1. Those who can cancel the map they have issued must have the burden of explaining the circumstances that are set out in the law and that the map was issued illegally and should not have been issued in the first place!
4.2. A landowner who complains that a decision made by a land administration body to cancel a map is illegal may file a lawsuit in court. Therefore, if the courts believe that the map was issued illegally, they can overturn the decision to cancel and order the map to be returned to the owner!
4.3. If a land administration has won a lawsuit in court and the map was issued illegally, the map cannot be canceled while that judgment is still in effect!
As can be understood from the above, canceling a map is not a measure taken by a landowner based on unpaid fines or service change fees!
Rather, it is only when there is a situation where it is believed that the ownership certificate was issued based on an illegal document or after the map was issued that the owner acquired possession of the land!
የአንድ ባለይዞታ ካርታ የሚሰረዘው
በምን ሁኔታ ነው?
1. የከተማ አስተዳደሮች የመሬት አስተዳደር አካላት የሚሰጡት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በዛ የመሬት ቁራሽ ላይ ባለካርታውን የተሻለ ባለመብትነት አመላካች ነው!
በፍ/በሔር ህጉ አንቀፅ 1195 መሠረት ካርታ የያዘ ሰው የቦታው ህጋዊ ባለይዞታ ተደርጎ ይገመታል።
ነገር ግን ይህ በህግ የሚወሰድ የባለይዞታነት ግምት በህጉ በተቀመጡ ሁኔታዎች ሊስተባበል የሚችል ነው!
2. አንድ ባለይዞታ ከሚመለከተው የመሬት አስተዳደር አካል የተሰጠው የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ሊሰረዝ ሊመክን ይችላል ወይ ወደሚለው ስንመጣ። ምላሹ አዎ ነው።
3. አንድ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የሚመክንባቸው ምክንያቶች ምንድን ናቸው?
የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የሰጠ የአስተዳደር አካል ካርታውን ማምከን መሠረዝ እንደሚችል ከፍትሐ ብሔር ህጉ አንቀፀሰ 1196 & 1197 መገንዘብ ይቻላል!
ነገር ግን በአንድ ቁራሽ መሬት ላይ ባለይዞታ ነህ ብሎ ካርታ የሰጠውን ሰው ባለይዞታ ካርታ ለማምከን የሚቻለው ካርታው ከመሠጠቱ በፊት የተፈጠረ እና ያለአግባብ ነው ባለካርታው የይዞታ ማረጋገጫውን ያገኘው የሚያሰኝ ሁኔታ ሲኖር ነው።
በሌላ አነጋገር ካርታ የሚሰርዝ አካል ካርታው ያለአግባብ መሠጠቱን የማስረዳት ሸክም አለበት!
4. ሰበር ሰሚ ችሎት ስለካርታ መሰረዝ የተለያዩ አስገዳጄ ትርጉሞችን ሰጥቷል።
ከነኚህም ውስጥ በመ/ቁጥር 42501 እና በመ/ቁጥር 99071 የሰጣቸው ተጠቃሽ ናቸው።
በነኚህ መዝገቦች የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመሬት አስተዳደሮች ከተማ አስተዳደሮች ባላቸው ካርታን የመሠረዝ ስልጣን ላይ ያሉ 3 መሠረታዊ የስልጣን ገደቦችን ግልፅ አድርጓል!
4.1. የሰጡትን ካርታ መሠረዝ የሚችሉት በህጉ የተቀመጡ እና ካርታው ከህግ አግባብ ውጪ ነው የተሰጠው አስቀድሞም መሰጠት አልነበረበትም የሚያሰኙ ግልፅ ሁኔታዎችን የማስረዳት ሸክም አለባቸው!
4.2. በመሬት አስተዳደር አካላት ካርታን ለመሰረዝ የተሰጠ ውሳኔ ህጋዊ አደለም የሚል ቅሬታ ያለው ባለይዞታ በፍርድ ቤት ከሰስ ማቅረብ ይችላል። ስለሆነም ፍርድ ቤቶች ካርታው የመከነው ያለአግባብ ነው ብለው ካመኑ የመሰረዙን ውሳኔ መሻርና ለባለይዞታው ካርታ ተመልሶ እንዲሰጠው መወሰን ይችላሉ!
4.3. አንድ የመሬት አስተዳደር በፍርድ ቤት ሙግት ከተረታና ካርታው የመከነው ያለአግባብ ነው ተብሎ ከተወሰነ ያ ፍርድ ፀንቶ ባለበት ወቅት ካርታውን ማምከን አይችሉም!
ከላይ ከተዘረዘሩት ለመረዳት እንደሚቻለው ካርታን ማምከን ባለይዞታ የሆነ ሰው ባልከፈለው የቅጣት ወይም የአገልግሎት ለውጥ ክፍያ መነሻነት የሚወሰድ እርምጃ አለመሆኑን ነው!
ይልቁንም የባለሀብትነት ምስክር ወረቀቱ የተሰጠው ከህግ ውጪ በማይፀና ሰነድ መነሻ ከሆነ ወይም ካርታው ከተሰጠው በኋላ ነው የመሬቱን ይዞታ ያገኘው የሚያስብል ሁኔታ ሲኖር ነው!
No comments:
Post a Comment
Note: Only a member of this blog may post a comment.