ቋንቋ ይወለዳል፣ ያድጋል ፣ ይሞታል ነው አሉ አማርኛ ግን ተበረዘ

ቋንቋ ይወለዳል፣ ያድጋል ፣ ይሞታል ነው አሉ አማርኛ ግን ተበረዘ
ስለ ሌሎች  የኢትዮጵያ ቋንቋዎች እንዴት እንደሆነ አላውቅም አማርኛ ግን በቃ ጠጅ መሆኑ ቀርቶ ብርዝ ሆኗል። የእንግሊዘኛ ቃላቶች ከነ ቁማቸው መግባታቸው ብቻ ሳይሆን  ካለ ቦታቸው መግባታቸው ነው። አንዳንዴ ሰው ፊት አማርኛ ሚስጢር ማውራት በምንም አይቻልም። እስኪ ለአብነት ያክል ይህን አባባል አንብቡትና ስንት እንግሊዝኛ ቃላት እንደተጠቅምሁ አስቡት።
ሬድ ይት ላይ ስቶፕ ሳላድርግ አልፌ ፖሊሱ ትኬት ሰጠኝ።
 እስኪ ይህንን በአማርኛ ልጻፍው።
ቀዩ መብራት ላይ ሳልቆም ስላለፍሁ ቅጣት አገኘሁ።
 በሌላም አርፍተ ነገር መጻፍ እንችለን።  ይህ ለአብንት ያክል ነው። ሌላው የአማርኛ መበላሽት እራሱ በራሱ ነው (self destruction)። ለምሳሌ ተመችኝ (comfort) ይምቻል,  ተመቸችኝ የሚሉት ቃላቶች የሚያገልግሉ ለእቃዎች  ለምሳሌ ለሶፋ ወንብር፣ ለአልጋ ወይም ለባርጩሜ ነው። እከሌ ተመችኝ፣ ሙዚቃው ይምቻል። ከእንግሊዘኛ ቃል መጣ  እንዳይባል ራሱ በእንግሊዝኛ ምቾት (comfort)  የሚያያዘው ከአካላዊ ምቾት ጋር ነው ለውስጣዊ ስሜት (ምቾት) ግን አይሆንም። ቢሆንም አገባቡ ለየት ያለ ነው። ታዲያ የዘመኑ አማርኛ ሲያጌጡ ይመለጡ ነው። ወዲያ..

Comments

Post a Comment