Shop Amazon

Tuesday, March 11, 2014

የቴለቭዥን ገንዘብ ልመና በርሃብተኛው ኢትዮጵያዊ ስም, አያናድድም?

ያገራችን ለማኝ 1 ብር አልቀበል አለችኝ

አይዟችሁ እረጋ በሉ። የኔው አመጣጥ ስለ ሃገሬ ለማኝ ሳይሆን በሃግሬ ድሃ ስም ስለሚንው ነው።
ልክ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረስሁ ነበር ይህ ያጋጠመኝ። ማጋነን ሳይሆን የእውንት ነው። ያው እንደተለመደው ዘመድ አዝማድን ከተገናኘሁ በሗላ አንድ ልጅ የያዘች ሴት ገንዝብ ጠየቀችኝ። እኔም ኪሴን ዳበስ አድርጌ ፭ ዶላር ጣል ሳደርግላት  "ምነው ባክህ ምን ላደርገው ነው ይህን በአውዳምት ምድር?" ብላኝ እርፍ እኔም ድንግጥ። ከዚያ አብሮኝ ያለው ወንድሜ (ከዚያው የሚኖረው) "ምንድ ነው?" አለኝ::
 ታሪኩን ስነግርው "ይች ጥጋብኛ ዶላር እምቢ አልች?" ሲል ለካን ሴትዮዋ አንድ ብር መሰሏት ኖሮ "እረ ጋሼ ይቅርታ እነዚህ እኮ ሲያዋክቡኝ ነው እባክዎ ይስጡኝ" አለች እኔም የእሷ አባባል ሳይሆን ያዘልችው ልጅ ሰላሳዘነኝ ሰጠሗት። ደስታዋ እሰከ አሁን ይታየኛል።
ግን እዚህ እኔ ያለሁበት ከተማ ለማኝ አለ? 
አለ? አለ ብቻ በያይነቱ ቀለም እንጂ ነጭ ጥቁር ቀይ ሴት ወንድ ህጻን እና በቴሌቪዥን። አዎ በቴሌቭዥን!
በቴሌቭዥን!


አዎ ይለምኑታል። የአገሬ ለማኝ ገንዝብ ለመለመን የማይጠራው ታቦት የለም። ግማሹ አውቆ ግማሹም ግድ ሆኖበት። የፈረንጁ የቴሌቭዥን ለማኝ ደግሞ የሚለምነው ታቦት እየጠራ ሳይሆን ድሮ ኢትዮጵያ ወስጥ ድርቅ ላይ ያነሱትን ፎቶ ይዘው ነው። ለስሙ እንሱ የሚሉት የምንለምነው ለነዚህ እርሃብተኞች ነው ይላሉ። አቤት ውሸት! አቤት ውሸት!  በቲቪ የምናየው መለመኛው ወንድማችን እኮ  እስካሁን ወይ ሞቷል ወይ ኢንቨስተር ነው ወይም ዲያስፖራ ወይም ሌላ ስለ እርሃቡም የሚያስታውሰው ነገር የለም ግን በስሙ ይለመንበታል። ታዲያ ለማኝ ስታዩ የኛ ብቻ ችግር እንዳይመስላችሁ:: ከልመና ያውጣን ነው ግን ልመና ደግሞ ቢዚነስ ነው!!
 

No comments:

Post a Comment