የዲይስፖራ ትርጉም ቅጥ አጣ።

የዲይስፖራ ትርጉም ቅጥ አጣ። በብዛት የሃገራችን የቋንቋ ትርጉም በባለሙያዎች የተመረኮዘ ሳይሆን አንድ ተዋቂ ሰው ቴሌቭዥን ላይ ወይም ራዲዮ ወይም ጋዜጣ ሊሆን ይችላል  ያንን ቃል ከተናገረ ወይም ከተናገረች ያ ቃል ትክክል ነው ብለን መደገም መደጋገም ነው። ለዚሁም ትልቁ ምሳሌ ዲያስፖራ ነው። ይህ ቃል የተሰጠው ሳይወዱ በግዳቸው ከሃገራቸው፣ ከቤት  ከቀያቸው በስደት በስው አገር ይኖሩ ለነበሩ እስራልያውያን (Jew) የተስጠ መጠሪያ ነበር። እዚህ ላይ ዋናውና ትልቁ ቃል " ሳይወዱ ብግዴታ" የሚለው ቃል ነው። ታዲያ ያ ቃል ለሁሉም በውጭ አገር ለሚኖር ኢትዮጵያዊ አያገለግለም። ለምሳሌ ለትምህረት፣ በዲቪ፣ ለጉብኝት፣ ለስራ፣ በልጆች ወይም በወላጆች የመኖሪያ ፍቃድ አግኝተው ከሃገር ፀሃይ ሞቋቸው ሰው አይቷቸው በቦሌ ሰተት ብለው የወጡት ዲያስፖራ አይደሉም። ታዲያ ማንው ዲያስፖራ? Well  እራሳችሁን ጠይቁ...


Comments