Shop Amazon

Saturday, March 22, 2014

ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ የIII (ሶስተኛ ) የአለም ጦርነት ዋዜማ ላይ ሳንሆን አንቀርም

ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ የIII (ሶስተኛ ) የአለም ጦርነት ዋዜማ ላይ ሳንሆን አንቀርም::


የሩሲያ ጦር ለዩክሬን ወታደሮች የክሪምያን አውሮፕላን ማርፊያ ለቀው እንዲወጡ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የሰጡ  ሲሆን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን አገሮች (NATO) አባላት የሩሲያው ፕሬዜዳንት በዚህ አያያዙ ከቀጠለ ሌሎችንም በአጠገቡ ያሉትን አገሮች እንዳይጎርሳቸው ሁሉም አባላት አገሮች ለመረዳዳት ውል ፈርመዋል። የህንን ውል ተግባራዊ ለማድርግ እና የሩሲያ አጎራባች አገሮች ከፍራቻ ለማውጣት የአሜሪካው ምክትል ፕሬ ዜዳንት ጆ ባይድን (Joe Biden) ወደ አውሮፓ ጉዞ አድርገው ነበር። ከአፍጋኒስታን ጦርነት በሗላ ብዙም ስራ ያላገኘው የኔቶ ሰራዊት አሁን ገና የሚያጣድፍ ስራ አገኘን ብሎ ወድ ሩሲያ ድንብር እየተጠጋ ሲሆን እንደ አንድ የኔቶ ጄኔራል የሩሲያው መሪ ልክ የመንደር አስቸጋሪ ጎረምሳ (Bully) ነው በማልት በፌዝ ሲናገሩ በአንፃሩ ደግሞ ፕሬዜዳንት ፑተን የኔቶን ወደ ራሽያ ድንበር ጠጋ ጠጋ ማለት ትንሽ ቅሬታ አስምቷቸዋል። ይህ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ ፑተን የድሮ የሩሲያ ግዛት አግሮችን ዋጥ ስልቅጥ ያደርጋቸዋል የሚልው ስጋት አሜሪካንና ሌሎችንም የአለም መንግስታትን አስግቷል። ይህ በዚህ እንዳለ የኢራን መንግስት ከእንጨት የተሰራ (እንሱ ነው ያሉት) ልክ የአሜሪካን ጦር ተሸካሚ መርከብ (Navy’s Nimitz-class carriers)በመስራት ላይ መሆኗን አንድ ሪፖርት በሳተላይት አየሁ ብሎ አስታወቀ። እንደ ዘገባው ይህ የውሸት የጦር ተሽካሚ መርከብ ሆን ብሎ በአሜሪካ ላይ ለማሾፍ ተብሎ የተስራ ነው ብሏል። ይህ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ ሶስተኛው የአለም ጦርነት ዋዜማ ላይ ያለን ይመስለኛል። ለሁሉም ያቅለው! AMEN

No comments:

Post a Comment