Shop Amazon

Saturday, April 26, 2014

የትኛው ደቀ መዛሙር (ሃዋርያ) ነው ኢትዮጵያ የሞተው?

የትኛው  ደቀ መዛሙርት(ሃዋርያ) ነው ኢትዮጵያ የሞተው?በቃ አንዳንዴ ሳያስቡት የሚሆን ነገር አጋጥሞውት ያውቃል? ያ ነበር ትናት በኔ ላይ የደረሰው::  ከቻናል ቻናል ሳማርጥ በቃ መፀሃፍ ቅዱስ (BIBLE) ከሚለው ሪሞት ኮንትሮሉ ክሊክ ክሊክ ካላደርግሁ አለ። ስፍራ ስቸር ጠቅ ሳደርገው የፊልሙ 10 ክፍል አለው። የመጣው ይምጣ ብየ ክፍል አንድን (ኦርት ዘፍጠረትን) ጀመርሁት።  ከዚያ  በኋላ የሆነውን ሆድ ይፍጀው ነው። በአስር ቀን የሚያልቀውን ፊልም በአንድ ሌሊት ላፍ አንድጌው ቁጭ። ፊለሙ እንደ ዶክመንተሪ ሆኖ የተሰራ ነው። ያላየሁት ነገር የለም።  አብርሃምን፣ ይሳቅን፣ እስማኤልን፣ ዳዊትን፣ ቅዱስ ገብሬልን፣ እመቤታችንና ልጇን እየሱስ ክርስቶስን ፣ ቅዱስ ሚካኤልን፣ መጥምቁ ዮሓንስን ፣ ሙሴን፣ ጳውሎስን፣  ጎሊያድን፣ በካፋን፣ እየሱስን፣ ሳምሶንን፣ ገሊላን፣ ቤተልሄምን፣ ናዝሬትን፣ ሶዶምና ጎሞራን፣ እዬሩሳሌምን፣ ቀይ ባህርን፣ ግብጽን፣ ሃናን ዮሴፍን፣  ንጉስ ሃሮልድን፣ ጎለጎታን፣  በቃ ሁሉንም አስመስሎ ያሳያል። ፊልሙ ውስጥ  የጌታን ታምር፣ ማን እንደከዳው፣ ማን እንደ ተከተለው፣ ማን አሳልፎ እንደሰጥው፣ ማን እንደፈረደበት ሁሉንም ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ፊልሙ የተሰራው በ2013 ነው። ፊልሙ ከኦሪት ዘፍጥረት ጀምሮ ትንሳኤን ያሳይና እንዴት አድርገው 12ቱ ሃዋርያት (ደቀ ሞዛሙርቱ) እንዴት የእግዚያብሔርን ቃል በአለም ላይ እንዳስፋፉ ይናገርና ከነዚህ 12 ደቀ ሞዛሙርቱ ውስጥ አንዱ ኢትዮጵያ ውስጥ ተገደለ ይላል። ይገርማል ይህንን ያለው ክፍል ፲ ላይ ልክ ሊያልቅ ሲል ነው። ይህንን ነገር ለእኔ አዲስ በመሆኑ የትኛው ደቀ መዛሙርት መሆኑን ከመናገሬ በፊት ጥያቄው ለእርስዎ እተወዋለሁ::ታዲያ የትኛው ደቀ መዛሙርት ነው? የጠላት ወሬ እንዳይሆን?

No comments:

Post a Comment