Shop Amazon

Wednesday, April 16, 2014

ፔት (pet) ዶሮ ወይም በግ

ፕት (pet) ዶሮ ወይም በግ

ከዚህ ከአሜሪካ አንድ ድረ ገጽ አለ ስሙ ክሬግስ ሊስት(craigslist)  ይባላል። ልክ ኮልፌ ተራ፣ መርካቶ፣ ፒያሳ ሁሉም ተደባልቆ እንደ ማለት ነው።ድረ ገጹ ላይ  አንዱ ቤት ያከራያል፣ ሌላው አሮጌ ካልሲ ይሽጣል፣ አንዷ እዩኝ ትላለች አንዱ ይህን እፈልጋለሁ ይላል ሌላው ስራተኛ ቀጣሪ አስቀጣሪ ነኝ፣ እንጨት ፈላጭ፣ ቀለም ቀቢ፣ አስተማሪ፣ ዘበኛ፣ ልጅ ጠባቂ በቃ ሁሉም አለ። ታዲያ አንድ ቀን በአጋጣሚ አንድ ሰው ዶሮ በነጻ እሰጣለሁ የሚል ማስታወቂያ አየሁ። በቃ  ቀይ ገብስማ ዶሮ። ወዲያው ደወልሁለት። የሚከተለው ቃላ ምልልስ ተደሮጎ ነበር። በአጭሩ
እኔ  “ሄሎ”
ባለ ዶሮ “ሄሎ”
እኔ “ማስታዎዊያ አይቼ ነበር ክሬግሊስት ላይ”
 ባለ ዶሮ  “የምን ማስታዎቂያ?”
እኔ” በነጻ የምትሰጥ ዶሮ”
 ባለ ዶሮ  “አዎ አለች”
እኔ “መውሰድ እችላለሁ”
ባለ ዶሮ “አዎ ግን አንድ ነገር ቃል ግባ”
እኔ “ምን?”
ባለ ዶሮ “ዶሮዋን መብላት አትችልም”
እኔ “ምን?”
ባለ ዶሮ  “አዎ ዶሮዋን መብላት አትችልም”
እኔ “ህም…”
ባለ ዶሮ  “አዎ ዶሮዋ ፔት (pet) ነች።  ግን አንቁላሏን ብቻ ነው መብላት የምትችለው”
እኔ ፔት የሚለው ድመት  ናት ነው የመሰለኝ
እኔ “እሺ”
ከዚያ የት እንደማስቀምጣት ግራው ሲገባኝ ሳላመጣ ቀረሁ።
ግን ፔት (pet) የሚለው ነገር ሁሌ  ያስቀኛል

ምክንያቱም እዚህ አሜሪካ (የሌላውን አገር አላውቅም) በግም ሆነ ፍየል ወይም ዶሮ አሳማማ መሆን ይችላል አንዴ ፔት (pet) የሚለውን ስም ካገኘ አይበላም አሉ። ፔት (pet) ማለት ልክ የእንስሳ ጓደኛ ማለት ነው። ከሁሉ ፈገግ ያደረገኝ ኢትዮጵያ  እያለሁ አስፈልፍየ አሳድጌ ትልቅ ሲሆኑ ያው ታርደው የተበሉት ፔቶቼ ናቸው። አዎ የለመዱት በግም ሆነ ዶሮ ሲታረድ ያሳዝናል ግን ያው ያለ ነው። ቻለው ቻለው አለ ዘፋኙ:: የአገራችን ዶሮወችና በጎች የዚህ የፔትን ነገር ቢሰሙ ለፋሲካ ስንት ዶሮውች ነፍሳቸው ይተርፍ ነበር። ግን የፔትን ነገር ያገራችን ዶሮችና በጎች አይስሙት ነው። ዳሩ ዋጋቸው ስለናር ሳንወድ በግዳችን ፔቶች ሆነዋል።

No comments:

Post a Comment