Shop Amazon

Monday, June 23, 2014

ወይ አቶ ሳምቡሳ in America





https://www.facebook.com/sambusaloveወይ አቶ ሳምቡሳ
ሳምቡሳ መነሻው የት እንደሆን አላውቅም። አረብ አገር፣ ህንድ ወይስ ከኛው አገር ኢትዮጵያ? ግን ከአሜሪካ እንዳልሆነ አውቃለሁ። ሳምቡሳ ስለምወድ የሳምቡሳን ፌስ ቡክ ባለቤት አድሪጌዋለሁ። ግን ዛሬ ከአቶ ሳምቡሳ ጋር አጋጣሚ ተገናኘን።ቦታውም አሜሪካ ውስጥ የሚገኘው ሱፕር ማርኬት ነበር:: ሳምቡሳ መልኩን አሳምሮ፣ አድጎና ሰፍቶ አንድ ሳህን አክሎ  ከምግብ ማሳያ መስታውቱ  (display box) ውስጥ ቁጭ ብሎ አይኑን ሲያጉረጠረጥ አይን ለአይን ተጋጨን። ወይ አቶ ሳምቡሳ? እኔም መስመሬን ጠብቄ ተራይን ሊደርስ  አንድ ሰው ሲቀር  ከፊቴ ያለው ሰው አቶ ሳምቡሳን አዝዞት ቁጭ። እኔም አፌን መያዝ ተስኖኝ ልክ ጠፍቶ የተገኘ ዘመዴን ያየሁ ይመስል  ሂሳብ ተቀባዩን(Cashier)  ሳንቡሳውን ለደንበኛው ከተቀመጠበት ሊያዎጣ ሲል ቀድም ብዬ
"ያ የምታወጣው ምግብ ስሙ ምንድን ነው?" አልሁት
ሰውየውም ኮራ ብሎ " ሳርቡሳ/Sarbosa" አለኝ
እኔም ክው አልሁ:: የኔን ስም አወላግደውም መጥራሩ አንሶ ደግሞ ሳምቡሳንም ያወላግዱት???ሰውየው ሳርቡሳ ያለው የኔውን ሳምቡሳ ነው። "የእኔ ስሜ ይጣመም" ብየ ሰውየውን  ትክክለኛ ስሙን ነገርሁት
ሰውየውም " ተሳስቼ ኖሯል? Did I pronounced wrong? " ሲለኝ
በተራዬ "አዎ ግጥም አድርገህ" አልሁት
ከዚያም የሚገዛው ፈረንጅ በሁኔታው ግራ ተጋብቶ
"አዎ ይህ ህንድ አገር የታወቀ ነው::" አለ
ባይገርማችሁ ወደ አምስት የሚሆን ገዝቷል። የኔም ጥያቄ ማለቂያ የለው። ለዚያ ገንዘብ ተቀባይ ትልቁን ጥያቄ ወርወር አደረግሁለት
ጥያቄውም "እናንተ ነው የስራችሁት? Do you guys prepared it?"
ሰውየውም እንደ ማፈር ብሎ  "አይ በረዶ ሆኖ ከሌላ ቦታ ነው የሚመጣው: It came as frozen from another place"  አለ
እኔም ልክ የማውቀው ሰው በረዶ ውስጥ በብርድ የተተዎ ሁሉ ፊቴ በሃዘን ተሞልቶ  "ምን?" አልሁት
ሰውየውም የፊቴን መለወጥ አዬ መሰለኝ
"ምንው ደህና አለኝ? Are you ok?"
እኔም ደህና ነኝ አልሁትና አከታትዬም እኔ ይህንን ሁሌ የኢትዮጵያ ምግብ ቤት ትኩሱን እበላለሁ አልሁት
እሱም  "ከሄት ነህ? Where are you from"  ሲለኝ አፌን ሞልቼ "ከኢትዮጵያ  Ethiopia" አልሁትና የት ትኩስ ሳምቡሳ እንደሚያገኝ ነገርሁት
ወይ አቶ ሳምቡሳ ምን አጠፋህ እስኪ በረዶ ውስጥ የሚያስቀምጡህ? ያንተስ ያንተ ነው ከአቶ እንጀራ ጋርም እንዲሁ እንዳንገናኝ። የዛኔ ምድር ቁና ትሆናለች። ከሁሉም ከሁሉም በቻይና የተሰራ (Made in China) እንጀራ ከሆነ::
ኤዲያ

No comments:

Post a Comment