Shop Amazon

Wednesday, July 2, 2014

የኢትዮጵያ ቶክ ሾው። (Ethiopian Talk Shows)


የኢትዮጵያ ቶክ ሾው።

 በአሜሪካ የቶክ ሾው (Talk show)ታሪክ ውስጥ እንደ አብነት የሚጠቀሱት ጆኒ ካርሰን (Johnny Carson)  ኦፕራ ዊንፍሪ (Oprah Winfrey) እና አርሰኒዎ ሆል (Arsenio Hall)  ለሎችም ይገኙበታል። ሌሎች ቅጅዎች ናቸው። በተለይም ደግሞ የጆኒ ካርሰንን ዘይቤና ዜዴ ያልቀዳ የቶክ ሾው ፕሮግራም የለም። እነ ጄ ላኖ (Jay Leno)፣ ዴቪድ ሌተርማን (David Letterman)፣

ካርሰን ዴሊ (Carson Daly)፣ ሌሎችም ቅጅዎች ናቸው። የነሱ ሲገርመኝ የቅጂ ቅጂ አገሬ ላይ ብቅ አለ። እኔ ሳላዬው ቀርቼ ነው እንጂ ብዙ ጊዜ የሆነው ይመስለኛል ግን ልክ ሳያስፈቅዱ የስሩት የችኮላ ስራ ነው የሚመስለው። የኔ ጥያቄ ምነው እውቀቱና ብልሃቱ ሳያንሰን ዘው ብለን የሌሎችን መንቸፍ እናደርጋለን? ከሁሉ ያሳቀኝ አዘጋጁና እንግዶች የሚጠጡበት የሸሃይ ስኒ። ይገርማል፣ እኔ እንደሰማሁት የፈረንጆች ቶክ ሾው ለእንግዶች ማበረታቻ እንዲሆን ቆንጆ አልኮል ያደርጋል አሉ። አይን መግለጫ እንዲሆን። የኛወቹስ?  ጠጅ? የአበሻ አርቂ? ጠላ? ያንን ካደረጉ ኦሪጂናሌ ሆኑ ይባላል። ዘፋኞችም ሆናችሁ አርቲስቶች እባካችሁ እራሳችሁን ሁኑ።  ቅጂ ምንግዜም ቅጂ ነው። ባለቤቱ ሌላ ነው እና። ምክር ነው የታዬኝን እንዳታኮርፉ

No comments:

Post a Comment