Shop Amazon

Monday, August 4, 2014

ልብሴን ነዎር በለው አሉ አለቃ ገብረሐና።





ልብሴን ነዎር በለው አሉ አለቃ ገብረሐና።
አለቃ ገብረ ሐና ብዙ ቀልዳ ዶች አሏቸው የዛሬው አመጣጤ ግን አንድ የፈረንጅ ቪዲዮ ካዬሁ በሗላ ነው። ነገሩ እንዲህ ነው, የቪዲዮ አላማ እንዴት ሰውን ልብ ብቻ በማዬት ግለሰቡን ለመርዳትም ሆነ ላለመርዳት ውሳኔ ማድርጋችንን የሚያሳይ ቪዲዮ ነው። ይህ ቪዲዮ ላይ አንዱን በረንዳ አዳሪ (homeless)  ቆንጆ ሱፍ (suit)  ልብስ አልብሰው እንዲለምን ሲያደርጉት፣ የለመነው ሰው ሁሉ  ገንዘብ ሲሰጠ አንዳንዱ ሃያ አምስት ሳንሲም (.25) ተጠይቆ አምስት ዶላር ሰጥቷል። ይህን ግለሰብ ግን ያው መደበኛ ልብሱን (ቆሻሻ ልብሱን) አልብሰው አንድ አይነት ቦታ ላይ እንዲለምን ሲያቆሙት አንድም ሰው ገንዘብ ጠብ አላደረገለትም። በጣም የሚያሳዝን ነው።

ይህ ግን የዘመኑ ሙከራ (Social Experiment) ሲሆን አባ/አለቃ ገብረሃና ግን ዱሮ ገና  ህዝባችንን ይህንን ሁኔታ ሞክረው ጨርሰውታል። ነገሩን ሰምታችሁት ይሆናል። 

" ከለታት አንድ ቀን አባ ገብረ ሃና ግብዣ ይጠራሉ፣ የዚያን ቀን በጣም ቸኩለው ኖሮ የስራ ልብሳቸውን እንደለበሱ ወደ ግብዣው ዘው ይላሉ፣ የድግ ዘበኛም አለቃን አላስገባ ይላቸዋል። አለቃም ዘበኛው አላስገባም ያላቸው ለምን እንደሆን ስለገባቸው ቤታቸው ሮጥ ይሉና የክት ጃኗቸውን ለብሰው ሲመለሱ ዘበኛው ካለምን ጥያቄ እጅ ነስቶ ያሰገባቸዋል፣ ከዚያም አለቃ እራት ሲቀርብ ምግቡንም መጠጡንም ልብሳቸው ላይ ይደፋሉ፣ ወዲያው በሁኔታው የተደነቀ ህዝብ አለቃይቃቸው አለቃም እንዲህ አሉ ይባላል። እኔ ሳልሆን ልብሴ ነው የተራው  አሉ ይባላል:: ይህ የአለቃ ድርጊት አሁን በቪዲዮ ቢሰራ በፈረንጆች ቋንቋ  (Viral Video) ይሆን ነበር። አይ አለቃ ከሁሉ ቀድመው የተማሩ አዋቂ ናቸው። "አዬ ሰው!" አለች ቀበሮ

No comments:

Post a Comment