Shop Amazon

Saturday, October 4, 2014

አርቲስት ጃኪ ጎሲ ስለዩቱቡ የፊያሜታ ቪዲዮ ላንቃ መዘጋት መግለጫ ሰጠ። ቪዲዮው ግን ዳብዛው ጠፋ





አርቲስት ጃኪ ጆሲ ስለዩቱቡ የፊያሜታ ቪዲዮ ላንቃ መዘጋት መግለጫ ሰጠ።
https://www.youtube.com/watch?v=MxCB354Druoሰሞኑን አወዛጋቢ ሆኖ የቆዬው ፉያሜታ በሚል እርእስ የተዘጋጀው የሙዚቃ ቪዲዮ ለምን አቶ ዩቱብ ድምጹን ጥርቅም አደረገው ስለሚለው አወዛጋቢም ሆን አጠያያቂ  ዜና እራሱ አርቲስቱ መልሱን ፍርጥርጥ አድርጎ ተናግሯል። እንደ አርቲስቱ አባባል ችግቱ ከዋናው ቪዲዮ ላይ ሳይሆን በመግቢያና በቪዲዮው መጨረሻ ላይ ባሉቱ አንፀባራቂና እንደ ነጎድጓድ በሚጮሁ መክፈቻና መዝጊያ ድምጾች ላይ ነው ብሏል። ያንን ችግርም ለመቅረፍ እነዚህን ቪዲዮዎችን ቆርጦ ማውጣት ሲሆን ዩቱብ አንዴ የተጫነን ቪዲዮ መቁርጥ በጣም አዳጋች ነው። ግን ሌላ ብልሃት አለ። አንደኛው አማራጭ ሌላ አዲስ ንፁህ ቪዲዮ መተካት ሲሆን ሌላውን ዘዴ ለግዜው ያዝ አድርገነው እራሱ ጃጂ ብልሃቱን ይጠይቅ። በዚህ አጋጣሚ እንደ አርቲስቱ አባባል የኤርትራ ወይም የደስተን ቪብር ዳንስ ስታይል የሚለው ዝም ብሎ ወሬ ነው ብሏል። ታዲያ ይህ ትምህርት ለአርቲስቶችና ለቪዲዮ አዘጋጆች እኔን ያዬህ ተቀጣ ነውና ነገሩ ግመል ሰርቆ ተጎንብሶ እንዳይሆን ጠንቀቅ ነው።
ይህንን  ሪፖርት ጽፌ ለንባብ ላበቃው ስል የጃኪ ጎሲን ቪዲዮ መለስ ብየ አዬሁት፣ ዛሬ ግን ላንቃው ብቻ ሳይሆን የተዘጋው ዳብዛው ጠፍቷል። የዚህን ቪዲዮ የይገባኛል ጥያቄ አቅራቢውም ግለሰብ ስሙ ወጥቷል፣ ስሙም   ፍፁም ዮሃንስ  ይባላል::አቶ ፍፁም እውነት ይህ ነገር ያንተ ብቻ ነው?


የአቶ ፍፁም ዮሃንስ ዮሃንስ ያቀረበውን የኔንት ጥያቄ ካዬሁ በሗላ ምርመራውን ቀጠልሁበትና ይህንን ሙዚቃ አገኘሁ እስኪ አዳምጡት።

No comments:

Post a Comment