ወንድማዊ ምክር ለወንድም ጃኪ

ወንድማዊ ምክር ለወንድም ጃኪ
ይህንን የፊያሜታን ጭቅጭቅ ለአንዱ  ወንድሜ ሳጫውተው  በነገሩ ምንም ሳይገረም  "እንደገና?" አለኝ። እኔም ግር ብሎኝ "ምነው?" ስለው ከዚህ በፊት ከአርቲስት ተሾም አስግድም ጋር ትንሽ መሻከር ነበር አሉ። ታዲያ ምነው ካልጠፋ ገጣሚና ዜማ አቀነባባሪ ጃኪ የራሱ የሆነ ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ወጥ ስራ ሰርቶ ኮራ ብሎ ማንምንም ሳይለማመጥ አይኖርም? የጠፋው ቆንጆ ድምጽ እንጂ ግጥምማ ሞልቷል። ከፈለገም ለመተባብር ዝግጁ ነን። ታዲያ ጃኪ በዚህ ሳይደናገጥ፣ ሸሚዙን ሰብሰብ አድርጎ፣ ኮፍያውን ጣል አድርጎ እና የሚጠመጥመውን ሻሽ ጠበቅ አድርጎ አመት ባልሞላ ጊዜ ስሙን የሚያጠፉትንም ሆነ የሱ ስም በመነሳቱ የተደሰቱን አንገታቸውን አስቀርቅሮ ለሚዎዱት እድምተኞች (FANS) ደግሞ ሞቅ ደመቅ ያለ ስራ ይዞ ብቅ ይበል። ምን ይመስላችኋል። " የሰው ወርቅ አያደምቅ ይላሉ" 

Comments