ገንዘብዎን ከቀማኞች እንዴት ያድናሉ?

አንዱ ደንበኛችን ደውሎ  እንደነገረን ትንሽ ቆይት ብሏል  አለ ችካጎ ውስጥ አንዱ የጉዞ ወኪል (ሶማሊያዊ ነው) ከመቶ ሰወች በላይ ለትኬት የከፈሉትን ገንዝብ ይዞ ጠፋ አለን። ሰዎቹ ለመሳፈር ሲሄዱ ትኬታቸው ባዶ ሆኖ አገኙት አሉ። ይህን እና መሰል ድርጊቶች እየተበራከቱ ስለመጡ አደራዎትን እራስዎን ይጠብቁ። ከዚህ በታች ያሉትን ነጥቦች ለትኬትዎ  ገንዘብዎን  ከመስጠትዎ በፊት በጥሞና ያርጋግጡ
፩ኛ ይህ ወኪል ለምን ያክል ጊዜ በስራ አለም ላይ ተሰማርቷል?
ከዚህ በፊት በወኪሉ የተታለሉ ሰዎች አሉ ወይ?
ትኬትዎን ሲቆርጡ ወዲያው አዬር መንገዱን ደውለው ትኬትው ትክክል መሆኑን ያርጋግጡ። ለምሳሌ የኢትዮጵያ አዬር መንድ ቁጥር  1800 445 2733 ነው። 
 ፬ ወኪሉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ አለው ወይ?
ወኪሉ  በህብረተሰቡ ውስጥ ለምን ያክል ጊዜ ቆየ?
ወኪሉ ከገንዘብ እና ከሰው የቱን ያስቀድማል?
ወኪሉ የሚሰጣችሁ ዋጋ በጣም ዝቅተኛ ከሆኑ እና በጥሬ ገንዘብ ብቻ ነው የምቀበለው ካለ ጠርጠር ነው። በብዛኛው የዋጋ ልዩነት ከ 20_100 ዶላር መብለጥ የለበትም
በክሬዲ ካርድ ሲቆርጡ የወሩ ሂሳብ ሲመጣ ገንዘቡን የወሰደው አዬር መንገዱ መሆኑን ያረጋግጡ።
ወኪሉ ሌላስ ከእምነት ጋር የተያየዘ ስራ ምን ይስራል?
"የስሙኒ ዶሮ የብር ገመድ ይዛ ጠፋች" እንዳይሆን ሀያ ዶላር አድናለሁ ብለው ሺ ዶላር እንዳያጡ ከሚታመን ወኪል ትኬትዎን ይቁረጡ
www.yebbo.com

ማሳስቢያ፥ የቦ የጉዞ ወኪል ከአዬር መንገድ ትኬት ውጭ ሌላ ብዙ የምንሳጣቸው አገልግሎቶች ስላሉ እነዚህንም አገልግሎቶ ለመስጠት ማንነታችን በፌድራል እና እስቴት ታሪካችን ተጠንቶ ከወንጀልና ማታለል ነፃ መሆናችን ታውቆ ሲሆን ከዚህም ሁሉ በላይ ደግሞ ፈጣሪ የምናከብርና ፈርሃ  እግዚያብሄ ያደረብን ወገናችንን በእምነትና በቅንንት ማገልግል አላማችን እና ግባችን ለድርጅታችንም ዋናው መሰረት ስለሆነ በስራችን ይተማምኑ።

Comments

Popular posts from this blog

What company has copoun in Groupon

እውነት ይሆን? ትራምፕ የመኖሪያ ፍቃድ ኖሯቸው ግን በመንግስ ድጎማ የሚኖሩትን ግለሰቦች ለማባረር እቅድ አለው እየተባለ ነው።

የዝንባቡዌ ዜጋ የሆኑት ጓድ መንግስቱ ሐይለማርያም ስለ ዝንባቡዌው ወቅታዊው ሁኔታ ምክር ለገሱ