Shop Amazon

Friday, January 9, 2015

የሰሜን ኮሪያው ፕሬዜዳንት ለምን በቃለ መጥይቅ (The Interview) በሚለው ፊልም በጣም ተቆጣ?






የሰሜን ኮሪያው ፕሬዜዳንት ለምን በቃለ መጥይቅ (The Interview) በሚለው ፊልም በጣም ተቆጣ?
ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ትናንት ከአንድ አባል ከሆንሁብት ትንሽ ሲኒማ ቤት ጎራ ብዬ ነበር። ፊልሙ የተለቀቀው በተወሰኑ ሲኒማ ቤቶች ስለሆነ በፈለጉብት ቦታና ሰአት ፊልሙን ማየት አዳጋች ነው። በዚህ ፊልም የተነሳ የሶኒ  ኮርፖሬሽን በኮምፒተሩ ላይ ዘረፋ ተካሂዷል። ማለትም በአካል ኮምፒትሮችን ሳይሆን በኮምፒተሩ ውስጥ ያለውን መረጃ በኢንተርኔት ላይ በመግባት ጥቃት የደረሰበት ሲሆን የኦባማ አስተዳደርም ለዚህ ጥቃት ብቸኛዋ ተጥርጣሪ ሰሜን ኮሪያ ናት ሲል የሰሜን ኮሪያም መሪዎች ከደሙ ንፁህ ነን ሲሉ ግ በአጠፋው ኦባማን ተሳድበዋል። ለዚህም መቀጣጫ እንዲሆን የኦባማ አስተዳደር በሰሜን ኮሪያ ላይ ተጨማሪ ማእቀብ ጥሏል።
 



ግን በአንድ ፊልም ምክንያት እንዴት ይህ ሁሉ ሊሆን ቻለ?
 ለመልሱ ከእኔው ጋር ቆዩ።
ፊልሙ የሚጀምረው አንድ የቶክ ሾው አዘጋጅ (James Franco ) በአሜሪካ ታዋቂ የሆነውን ኤም ኤን ኤምን  Emine ቃል ምልልስ ሲያደርግ ነው።   የዚህ የቶክ ሾው ፕሮዱዩሰር (Seth Rogen) ጠቃሚና እውነተኛ የጋዚጠኛ ስራ መስራት እንጂ ይህንን ቱሪ ናፋ ፕሮግራም ለማዘጋጀት በጣም የታከተው እንደሆነ ተናግሮ የቶክ ሾው ሆስት እና ፕሮዲዩሰሩ የፕሮግራሙን ይዘት ለመቀየው ተስማምተው ይለያያሉ።
መርዝ  የያዘው ሻንጣ

እዚህ ላይ ነበር የሰሜን ኮሪያው መሪ የህንን ሾው (Skylark Tonight ስካይላርድ) እንደሚወድ ከሆነ ብሎግ ላይ ያነበቡት። ይህንን ታላቅ ዜና እንዳነበቡ ነበር ያልታሰበውን ትልቅ እቅድ ያወጡት። ያም እቅድ እራሱ ኪምን በዚህ ቶክ ሾው ላይ ቃለ መጠየቅ ማድርግ ነበር። ከዚያ የቶክ ሾው ፕሮዲዪሰር ለሰሜን ኮሪያው ቤተ መንግስት ስልክ ደውሎ ፕሬዜዳንት ኪምን ማነጋግር (ቃለ መጠይቅ) እንደሚፈልግ የተናገረው። ወዲያው ያልታሰበ ታላቅ ዜና ደረስ። ፕሬዘዳንቱ ፈቃደኛ እንደሆነና የቶክ ሾው ሆስት እና ፕሮዲዩሰሩ ወደ ሰሜን ኮሪያ እንዲመጡ ይጋበዛሉ።
ከኪም ጋር ፊት ለፊት

 እዚህ ላይ ነገሩ ሁሉ ከቶክ ሾው ወደ ፖለቲካ የተቀየረው። የሰሜን ኮሪያ ፕሬዘዳንት የዚህ ቶክ ሾው እንግዳ መሆኑን በተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች ተለፈፈ፣ ተነገረ እንዲሁም ተዘገበ። ይምህ ዜና ላልታሰበው የአሜሪካው የስለላ ድርጅት ሲአይ ኤ ( CIA) ደረስ። ሲአይ ኤም የቶክ ሾው ሆስቱ የሰሜን ኮሪያውን ፕሬዜዳንት እንዲገድል ተነገረው። አልፈልግም ብሎ አንገራገረ ግን አሳመኑት። ፕሬዘዳንቱንም የሚገልው በጥይት ሳይሆን በመርዝ ነው። መርዙ በቶክ ሾው ሆስት ስካይላርክ መዳፍ ላይ በፕላስትረ የጣበቃል ከዚያ የፕሬዘዳንቱን እጅ ሲጭብጥ መርዙ በፕሬዜዳንቱ ቆዳ አድርጎ ወደ ደም ስሩ ገብቶ አሰቃይቶ ይገለዋል። በዚህም እቅድ ተስማምተው መርዝ ያለባትም ፕላስተር ከሻንጣው ወስጥ ደብቆ እንዲሄድ የነገረዋል። ነገር ግን ሲአ ኤ የሰጠው ሻንጣ በጣም የሚያስጠላ ስለነብረ አቶ ስካይላርክ (ሆስት) የራሱን ውድ ሻንጣ ይዞ መርዟን ግን ከማስቲካ ጋር አድርጎ ወድ ሰሜን ኮሪያ ይበራል።
ለነዚህ ሁለት ግለሰቦች (ሆስትና ፕሮዲዪሰር) ሲ አ ኤ የክንድ ሰዓት ሰጠቷቸዋል





ጥበቃ አባሉም ማስቲካውን (መርዙን) ዋጥ ያደርገዋል።
ከዚያም ቤተ መንግስት ደርሰው ፍተሻ ሲደረግ የፕሬዘዳንቱ ከፍተኛ የጥበቃ አባሎች ማስቲካውን ከሻንጣው ውስጥ ያገኛሉ ከዚያ አንደኛው “ይህ ምንድን ነው?” ብሎ ሱጠይቅ አቶ ስካይላርክ “የህማ ማሲካ ነው“ ይላል። የጥበቃ አባሉም ማስቲካውን (መርዙን) ዋጥ ያደርገዋል። መርዝ ነው እንዳዩሉ ጨንቋቸው በአይናቸው እየተጠቃቀሱ አጠገባቸው መርዙ ተበላ። ከዚይም የጥበቃ ሰው ይህ ማሳቲካ ሳይሆን አር አር የሚል ነው ብሎ ማቲካውን ይተፈዋል። ግን ምን ዋጋ አለው መርዙ ስራውን ጀምሯል። 

ከዚያም ከፕሬዜዳንቱ ካር ይገናኛሉ። ከተሰነባበቱም በሗላ አሜሪካ ላለው ሲ አ ኤ መርዙ በጥበቃ ሃይሎች እንደተበላ እና ሌላ መርዝ እንዲልኩ ይነገራቸዋል። ሲ አ ኤም ሌላ መርዝ አስጋጅተው በአብራሪ አልባ (DRONE) ድሮን ይልካሉ። እዚህ ላይ ያልነገርሗችሁ ለነዚህ ሁለት ግለሰቦች (ሆስትና ፕሮዲዪሰር) ሲ አ ኤ የክንድ ሰዓት ሰጠቷቸዋል። ይህ ሰዓት ስልክና ጂፒ ኤስ ያለው ሲሆን በማንኛውም ቦታ ሆነው ማውራት ይችላሉ። ከዚያ ድሮኑ አዲስ መርዝ ይጥልላቸወል (ብዙ ትይንት አልፋለሁ)
አቶ ስክይላርክ እና ፕረዜዳንቱ በጣም ይቀራረባሉ:: የታንክ ጨዋታ


አቶ ስክይላርክ እና ፕረዜዳንቱ በጣም ይቀራረባሉ። ማውራትና መጠጣት እንዲሁም መባለግ ይጀምራሉ። አንድ ቦታማ ይሳሳማሉ:: ይህንን ደግ ፊት ያዬው የቶክ ሾው ሆስት ፕሬዘዳንቱ በጣም የዋህ ስለሆነ አልግደለም ብሎ ወሰነ። ግን የቶክ ሾው ፕሮዲዩሰር ፕሬዘዳንቱ በጣም እስስት ስለሆነ አሁን የሚያሳዬው የውሽት ፊት ነው ቢለው ለመስማት ተሳነው ። አገሩቷ በርሃብ የተሰቃየች፣ ብዙ ዜጐቿ በእስር ያሉ፣ ፕሬዘዳንቱ በጣም አምባ ገነን ከመሆኑ የተነሳ ህዝቡ እንደ ፈጣሪ የሚያየው እንዲያውም ህዝቡ በጣም እንደ ልዩ ፍጡር ስለሚመለከተው ሽንት ቤት እንኳ ሄዶ ካካ እንደማይል እና የካካ ቀዳዳ እንደሌለው የሚያምን መሆኑን ይነግረዋል። የቶክ ሾው ሆስቱ ግን በፕሬዘዳንቱ በተደረገለት ታላቅ አቀባበል ልቡ ስለረካ ለመግደል የተሰጠውን መርዝ ውሃ ውስጥ ይጨምረዋል። በዚህም በጣም የተናደደው የቶክ ሾው ፕሮዲዩሰር በቀረችው አንድ መርዝ እራሱ  ኪምን  ለመግድል ይወስናል። ለመግድል ሲሞክርም የቶክ ሾው ሆስት ኪምን ያድነዋል። ይህ በዚህ እንዳለ የቶክ ሾ ሆስቱን ፕሬዘዳንቱ ከካቢኔቶቹ ጋር እራት ይጋብዘዋል። ያ ኔ ነበር የፕሬዘዳንቱ ማንንት በጉልህ የወጣው። 


የቶክ ሾ ሆስቱን ፕሬዘዳንቱ ከካቢኔቶቹ ጋር እራት ይጋብዘዋል
ከኪም የፕሬስ ክፍል ሃላፊ
አቶ ስክይላርክ (ቶክ ሾው አቅራቢ) በእራቱ ላይ ያ ልክ እንደ ህፃን ልጅ ሲፍለቀለቅ የነበረው ኪም ትርሽ  ጭራቅ መስሎ ታዬው። ወዲያው ከእራቱ አቋርጦ ከተማውን ሲቃኝ ፕሬዜዳንቱ አገሬ ጥጋብ፣ ሰው የፋፋ ህዝቡ እና  በጣም ደስተኛ ብሎት የነበረው ት ዝ አለው። በአጋጣሚ በፍራፍረዎች ወደ ተሞላ ሱቅ አይኑ ዘው አለ። በመስኮት ሲመለከት ቆይቶ ወድ ውስጥ ገባ አለ። በሩ  አክተቆለፈም ነበር:: ለካን በፍራፍረ ታጭቆና ተንሸቁጥቁጦ የታየው ሱቅ የተሞላው በፕላስቲክ የተሰሩ የውሸት ሙዝ፣ ብርቱካን ፣ሲማቲምና ሌሎችም አትክልቶች ሆነ ተበሎ ተመልካችን ለማደናገር ተብሎ የተሰራ ነው።

በዚህ የተናደደው አቶ እስካይላርክ ወደ ክፍሉ እየጋለበ ሄደ። ጓደኛው (ፕሮዲወሰር ) ከክፍሉ ብቻውን ነበር። ነገር ግን ከዚህ በፊት ያልነገርሗችሁ ከኪም የፕሬስ ክፍል ሃላፊ ጋር በጣም ተዋደው ነበር። እሷም ሆን ብላ ብቻውን እንደሚሆን አውቃ ስለሚቀጥለው ቃለ መጠይቅ ለመንጋግር ነው ብላ ክፍሉ ገብታ ኖሮ ሳያስቡት በፍቅር አለም ነጉደው ያገኛቸዋል። የአቶ ስካይላርክን በድንገት መምጣት የደነገጡት ፍቅራቸውን ሳይጨርሱ ሴቷን በብርድ ልብስ አልብሶ እንድትደበቅ ያድርጋታል። አቶ ስክይላርክም ክፍሉ ውስጥ ከስራ ባልደረባው ውጭ ሌላ ስው የለም ብሎ ኪምን መግደል እንደሚፈልግ ይስማማል። ይህንን የሰማችው ብርድ ልብሱ ውስጥ ተደብቃ የነበረቸው የኪም ፕሬስ ክፍል ሃላፊ ተፈንጥራ ትወጣለች። በሁኔታው ግራ የተጋባው ስክይላርክ ምን እያደረገች እንደሆን ይጠይዋል:: ጓደኛውም እሷም በነሱ ሃሳብ እንደምስማማ እና እንደምትትባብር ትገልጻለች። ግን ኪምን በመርዝ ከመግድል በቃል መግደል ጥሩ እንደሆን ይስማሙና ቃለ መጠይቁን ለማድርግ የወስናሉ።





 አቶ ስካይላርክም የሚሰጠው ቃለ መጠይቅ ቀድሞ የተፃፈ (ስክሪፕትድ) ስለሚሆን እንደፈለገ መጠየቅ አልችልም ይላል። የፕረስ ሃላፊዋም እኔ ስለሆንሁ የምቆጣጠረው የፈልግኽውን መጠየቅ ትችላልህ ትልዋልች። ከዚህ ቃለ መጠይቁ ይዘጋጃል። ይህ ቃለ መጠይቅ በጣም ሲጠበቅ የነበረ ስለሆን በአጠቃላይ የአለም ህዝብ በተለይም ደግሞ የሰሜን ኮሪያ ህዝብ በጉጉት የሚጠብቀው ነበር። አላማው ፕሬዜዳንቱን ማሳላቅ፣ ማዋረድ እና መሳቂያ ማድረግ ነበር። የህን ሴራ ልብ ያላለው ኪም ሞቅ ደመቅ ብሎ ለቃለ ምልልሱ ቀረበ። ሕዝቡም ቴሌቭዥኑን ከፈተ። ኪም ሳቅ አቶ ስካይላርክ የውሽት ፈገግታ ይዘው መድረኩን ያዙት። ኪም የሚወዳት ውሻውን ለስካይላርክ ሰጠው። ከዚያ ነበር ታላቁ ቃለ መጠይቅ (The Interview)እውን የሆነው።
የመጨረሻዋ ትንፋሽ

ኪም ያላሰበው ጥያቄ ዱብ አለበት። ኪም አሜሪካ እና መሰል ጠላቶች ክፉ እያወሩበት እንጂ አገሩ ጥጋብ፣ ገበያው አማን ህዝቡ ደግሞ ሰላም ነው አለ። አቶ ስካይላርክም አሜካን ነቀፈ (አውቆ) ከዚያ ነበር ስካይላክ ኪምን ለምን ህዝብህ ይህንን ሁሉ መከራ ከቻለ እንዴት ዋጋውን ደህና አድርገህ አትከፍልም ያለው። ያኔ ነበር    


ይቀጥላል...

No comments:

Post a Comment