ባወጣው ባወርደው ሁሉም ነገርበሳት ከመቃጠል፣ አንገት ከመታርድአገር ላይ መለመን እንዴ ጣሙ ያምር።


ባወጣው ባወርደው ሁሉም ነገር
በሳት ከመቃጠል፣ አንገት ከመታርድ
አገር ላይ መለመን እንዴ ጣሙ ያምር።እባካችሁ በደቡብ አፍሪካ እና በአረብ አገር ያላች ሁ ወገኖች ወደ አገራችሁ ተመለሱ
ይህ ሳምንት በመላው የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ  ጥላሸት የለበሱ ሳምንታት ተብሎ የሚጠራ ሳምንት ነው። የደቡብ አፍሪካው ዙሉ ሲገርመኝ የሊቢያው አይሲስ ተጨመረበት። ስፈራ ስቸር ቪዲዮውን ክሊፕ አይቼ የደረሰው ነገር በአይኔ ቀኑ ሙሉ ሲንከራተት ዋለ። ግን ምን ላድርግ? አቅሙ ጠፋኝ። በቃ የተቅበዘበዘ ቀን ነው። ወገናችን ልክ ነፋስ እንደነካው አበቅ ያልገባበት የለም። ግማሹ ያለው ከአንበሳ መንጋጋ ስር ነው። ይህ በዚህ ስምንት የደረሰው ነገር ማለቂያ የለውም፣ ገና ጀመር እንጂ። ለእኔ የሚታየኝ አይኑ እያዬ እንደ በግ ከሚታረድ ወገኔ  አገሩ ላይ በሰላም ለምኖ መኖር ይሻላል። ታዲያ ከአገር የወጣው ወገኔ በፖለቲካም ሆነ በኢኮኖሚ ሁሉንም ነገር ጣል አድርጎ ጉዞ ወደ ቤት ነው። አወ ለተቀማጭ ሰማይ ቅርብ ነው ግን አሁን ባለኝ አቅሜ ማድረግ የምችለው በሃሳብ እንኳ መርዳት ስለሆነ። ጉልበት እና ደራሽ የላቸውም ብለው ከሚጨርሱን የአገራችንን አዬር ተንፍሶ መሞት ታላቅ ክብር ነው።

Comments

Popular posts from this blog

Birhanu Nega scapped death

What company has copoun in Groupon

የአሜረካው ስታር ባክስ ኩባንያ በአሜሪካ ለሚገኙ ኢትዮጵያውን በነፍስ ወከፍ 50ሺ ዶላር ካሳ ለመክፈል ተስማማ