Shop Amazon

Thursday, April 30, 2015

የISIS VIDEO ውሽት ወይስ እውነት?





የISIS (Islamic State of Iraq and the Levant)VIDEO  ውሽት ወይስ እውነት?

የራሳችን ጥናት:- የመጀመሪያው ቀን ወንድሞቻችን የተሰውበትን ቪዲዮ ለማየት ጉልበቱም፣ ድፍረቱም አልነበረም፣ እየቆየ ሲሄድ ግን ሂዎታቸውን  በደቂቃዎች (frame by frame) አሟሟታቸውን በፊት ያለውን  አንድ ባንድ እየቃኘነው ነው። ከስንት ፍለጋ በሗላ በጣም ጥርት ያለ ቪዲዮ (HD VIDEO) አግኝተናል። ታዲያ አንዳንድ ሚዲያዎች እንደሚሉት የውሸት አይመስለኝም። ግን እስክ አሁን ያልገባኝ ልጆቹ ያላቸው እርጋታ እና ዝምታ ነው። በቃ ህልም ላይ ያሉ ይመስላል። የሰጧቸው ማደንዘዣ አለ መሰለኝ። በተለይ ጥቁር ከለበሱት ውስጥ ከመሃል ካሉት በስተግራ በኩል ያለው ልጅ በሰመመን ወይም በእንቅልፍ ላይ ያለ ይመስላል። በቃ ቀና እያለ ሰውየው  (ገዳዩ) ሲናገር ቀና ብሎ ያይና መለስ ይላል። እንደሚመስለኝ የሰጡት ማደንዝዣ አንሶ ወይም መንቃት ፈልጎ ይመስላል። አይኑ በቃ እንቅልፍ ላይ ያለ ይመስላል። 

ከመሃል በቀኝ በኩል ያለው ልጅ ይናገራል። የሚያማትብ ይመስላል ከንፈሩን ይነክሳል። 

ከነዚህ ሰማእታት ጋር አብሮ የተሰዋው እስላሙ ወንድማችን ልዩ ምልክት ያለው ይመስላል። ግንባሩ ላይ ከፀጉሩ መጀመሪያ ላይ እና አፍንጫው ላይ ለምጥ አለበት። ይህንን ምልክት ያስታውሱ። 

ሌላው የጥቁር ለባሾችን ይዞ ከጫካው ሲወጣ የሰልፉ መሪ የነበረው ልጅ ፀጉሩ ዞማ ሆኖ በንፋስ  የሚበተን ነበር፣ ነገር ግን ለሞት ሲያዘጋጇቸው በግራ በኩል መጀመሪያ የነበረው ልጅ ፀጉሩ አጭርና ፂም  ያለው ልጅ ነው። 


የቢጫ ለባሾችም በሰልፍ ያሉት እና የታረዱት ይለያያል። እስካሁን ፍራቻው ስላለቀቀኝ ሲታረዱ ያለውን ቪዲዮ እዘልዋለሁ እንጂ ለማዬት በጣም ይሰቀጥጣል። 

እንዲሁ ሁለት ጥቁሮች (ገዳዮች) አሉ። ቅጥነታቸውና እርዝመታቸው የኢትዮጵያዊ  ነው ከሚባለው ይልቅ ሶማሌ  ይመስላሉ። እጃቸው በጣም እረጅምና ቀጭን ነው። አሁንም ጥናቱን እንደቀጠልሁበት ነው። መቼ እነሚያልቅ ግን ፈጣሪ ይወቀው። 

ይህንን ጥናት ሳደርግ ከዋናው አይሲስ ድር ገፅ ሳይሆን አይቀርም የደረስ ሁት። ድር ገፁ በቃ በየ ቀኑ  ቪዲዮ ያወጣል። አይጣል ነው። ለምሳሌ ዛሬ ሁለቱን ሰወች ጭንቅላታቸውን በቡክሌት ፈጥፍጠው ሲገድሉ ትናንት ደግሞ አንገታቸውን የእንጨት ትራስ አንትርሰው በጎራዴ ቀሏቸው። ይህ ሁሉ ሲሆን ገዳዮች ፊታቸው ይታያል ህፃናት እና ሴቶች ከበው ያያሉ። በጣም ዘግናኝ ግዜ ደረስን። ለምሳሌ ባላፈው ጊዜ ትሪፑሊ ሊቢያ ላይ አንዱን ከተማ ሲያጋይ እዚያው ቆሞ ቪዲዮ ይቀዳል። 

 የናንተም የኔም ጥያቄ ይህ ቪዲዮ እውነት ነው ውይ ነው? ሰሞኑን በ አደባባይ የራሳቸውን ዜጋ ሲገድሉ ካዬሁ በሗላ ይህ ቪዲዮ ውሽት መሆኑን መጠራጠው ሳይሆን ይህንን ቪዲዮ ለመስራት ሌሎችም ሰወች ሳይሞቱ የቀረ አይመስለኝም። ይህ ቪዲዮ በጣም ለማስፈራሪያ ሆኖ እንዲሰራ ስለታሰበበት ሌሎችም ብዙ ሰወች ሰለባ የሆኑ ይመስለኛል::

Al Furqan logo

al-Furqān Media presents a new video message from The Islamic State: “Until There Came To Them Clear Evidence”

The US Treasury Department added the Al Furqan Foundation Welfare Trust to the list of terrorist entities today. Al Furqan, which is based in Pakistan and Afghanistan, funds al Qaeda, Lashkar-e-Taiba, and the Taliban, and has been directly linked to a notorious jihadist who is a leader in both al Qaeda and the Taliban.
Treasury added Al Furqan to the US list of Specially Designated Global Terrorists. A State Department press release on the designation noted that the move was made along with the Saudi government, which listed the group “under its Law of Terrorism Crimes and Financing and the Royal Decree A/44.”

 የቪዲዮው አዘጋጅ የሚገኘው ሶሪያ ነው ያቤት የሚመስል አርማ ያለበት ደግሞ የ አይሲስ ተከታይ ድርጀት ሲሆን በአብዛኛው ጥቁር ቱታ የለበሱትን የገደለውን ያሳያል። ይህ የሚያሳዬን ወንድሞቻችን በሁለት ቡድን የተገደሉ ሲሆን ቪዲዮውን ለማጠናቀር ሶሪያ ተልኮ የተሰራ ይመስለኛል የምህም ማለት ይህንን ቪዲዮ ሰርቶ ለማጠናቀቅ ሳምንታት ብልም ወራት ይወስዳል።  እኔ ባደረግሁት ጥናት መሰረት ለአይሲይ ቪዲዮውን የሚሰራው ኩባንያ በጣም የተደራጀና ልክ ሆሊ ውድን የሚስተካከል ኩባንያ ነው። እንደሚመስለኝ ከስልሳ አምስትሺ በላይ የድረ ገፆችን የሚያስተናግድ ሲሆን የሚሰሩት ቪዲዮውች በሶስት ይከፈላሉ የመጀመሪያው ደጋፊ ለመሰብስብ ሲሆን ሌላው ደግሞ ለማስፍራርት እና ለመመልመያ አገልግሎት  ይውላል።

ሌላው በዚህ ጥናቴ  ቪዲዮውን ማን መጀመሪያ ለኢንተርኔት ለቀቀው ሲሆን ይህንን ያዘጋቸው ማን ነው የሚለው ነው። በቪዲዮው ላይ ከላይ በኩል በግራ ወይም በቀኝ የ አይሲስ አርማ ያለ ሲሆን ለላ ቤት የሚመስል አርማ ያለበት አለ እንዲሁም ቪዲዮው ሲጀምር ልክ የ አልጃዚራን ምልክት የሚመስል  ሎጎ  አለ።

No comments:

Post a Comment