ኢትዮጵያና ክብሯ
ከዚህ ቪዲዮ ላይ እስኪ በየትምህርት ቤቱ የሚማሩትን ኢትዮጵያውያን ተመልከቱ:: ሁሉም ተምሮ ወደ አገሩ ሄዶ ህዝቡንና አገሩን ለመርዳት ያለውን ፍላጉት።
ታዲያ ይህንን ቪዲዮ አይተው ከጨረሱ በኋላ ጃንሆይ ከስልጣን ከወረዱ በኋላ የኢትዮጵያውያንን ሂዎት ያጢኑ። አዎ በዘጠና ፐርሰንት (80_90%) የምንሆነው ኢትዮጵያውያን ይህንን ጽሁፍ የምናነበው በሰው አገር ሆነን ነው:: ዛሬ በቦሌም ሆነ በሞያሌ በዲቪም ሆነ በሌላ አድርጎ አገሩን ለቆ በሰው አገር ለመኖር ያቆበቆበው ህዝብ ስናይ ምነው ያ ጊዜ ተመልሶ በመጣ ያሰኛል። ዛሬ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በየ አረቡ አገር ሂዎታቸው ከውሻ በታች ሆኖ ግማሹ እንደበግ ይታረዳል፣ ከባህር ይሰምጣል፣ ከፎቅ ይወረወራል፣ ከነ ነፍሱ ይቃጠላል ሌላ ሌላውም በምድር ላይ ያለ ግፍ ይደርስበታል። ታዲያ የጃንሆይን ዘመነ/ጊዜን የምትተቹ ካላቻሁ እናንተ ከዚያ የተሻለ ጊዜ አምጥታችኋል ወይስ ለማምጣት አስባችኋል? አይመስለኝ፣ምክንያቱም 40 አመት ጠበቅሁ ሁሉም ያው ነው:: እኔ በበኩሌ የምመኘው ምነው ቀደም ብየ ተውልጄ ሂዎቴን በሙሉ በጃንሆይ ጊዜ በኖርሁ ነበር። እርስዎስ? ከተስማሙ ለሌሎችም ያካፍሉ:: ዘረኞች፣ፐለቲከኞች፣ አወቅን ባዮች በጃንሆይ ጊዜ የነበራንን ክብር መልሳችሁ ካላመታጣችሁ በስተቀር የናንተ እውቀት ገደል ይግባ :: ኤዲያ "little knowledge is danguerouse" አለ ፈረንጅ እውነቱን ነው:: ጃንሆይን ከስልጣን ያወረዳችሁ ሁሉ ነፍሳችሁ መቀመቅ ይውረድ
No comments:
Post a Comment