የኔ ከተማ ቢራ ቤት ጠላ ቤት ሆነ

የኔ ከተማ ቢራ ቤት ጠላ ቤት ሆነ
ነገሩ እንዲህ ነው። ያኔ ዱሮ ጠላ ጠላ እዬነበር ታስታወሳላችሁ። እንግዳ ሲመጣ በማንቆርቆሪያ ጠላ ግዙ ስንባል መጀመሪያ ቀምሰን ከዚያ ልክ እንቁላል እንደያዘ ዘንቢል ጠላው ተንቅንቆ እንዳይደፋ ቀስ ብለን ስንራምድ ያ ዛሬ አሜሪካ አገር ሳላስበው መጣ። በዚህ እኔ ባለሁበት ሰፈር ላይ መንገዱን ይዞ በቃ የተለቀቀ ቤት ሁሉ የቢራ መጥመቂያ ሆኗል። በእንግሊዘኛው አጠራር ማይክሮ ብርዎሪ  (Micro Brewery) የሚሏቸው ቤቶች በቃ በየቀኑ ብቅ ብቅ እያሉ  የትላልቅ የቢራ ፋብሪካዎችን ገበያ እየተሻሙ ነው። ብታምኑም ባታምኑም የነዚህን ጠላ ቤቶ (ቢራ ጠማቂዎች) ቢራ ከነገፈታው ፉት ለማለት አንዳንዴ ጠጪው አውቶቡስ ሙሉ ተከራይቶ ይመጣል። በተለይ ደግሞ ከኔ ጎን ያለው ቤት ለየት እና ሰፋ ያለ ነው። ከውጭ ሆኖ የቢራ መጥመቂያው ጋኖች ወለል ብለው ይታያሉ፣ በሳምንት አንድ ቀን ብቅል ሲጨመር ነው መሰል መንደሩ ሁሉ ልክ ብቅል ብቅል ይሸታል፣ በበርሚል በበርሚል ሆኖ የታሸገ አተላ ለመውሰድ የሚመጡ መኪኖች ድሮ አገሬ እያለሁ ለከብት ብለው የምንሸከመው አተላን አስታወሱኝ። ከዚህ ቢራ ቤት ቢራ ክፈትልኝ ሳይሆን ቅዳልኝ ነው። ልክ እንደ ድራፍት ቤት ቢራው እንደወረደ ይቀዳል። የተለለያዬ ቢራ ስላለ ብትንሽ በትንሹ መቅመስ ይቻላል። ሌላው እስከ ዛሬ አሜሪካ ያላዬሁት በፌርሙስ ፣ በጠርሙስ ወይም በማንቆርቆሪያ ቢራ ገዝተው ቤታቸው ለመጠጣት የሚገዙትን ሰውች ነው። በዚህ አገር ህግ መንገድ ላይ ቢራ ይዞ መዞር ስለማይቻል ሁሉም ከጠጣ በሗላ ወደ ቤቱ ይዞ ይሄዳል። ጨዋታው የደራ ሁሉም ደስተኛ ይመስላል። ልክ የ አገራችንን ጠላ ወይም ጠጅ ቤት ይመስላል። በነገራችን ላይ የነዚህን ቢራ ጠማቂዎች ስራ ለማስፋፋት የካሊፎርንያ መንግስት በጣም እገዛ እያደረገ ሲሆን በየቦታው የቢራ መቅመሻ ቦታዎች ሊዘጋጁ ነው። የቢራ መጥመቅ ባህል በጣም ተፈላጊነቱ እያዬለ በመምጣቱ በሳንድያጎ ከተማ የሚገኘው የሳንድያጎ ስቴት ዪኒቨርስቲ በማስተርስ ደረጃ የጠላ፨የቢራ መጥመቅ ዲግሪ እየሰጠ ነው። በነገራችን ላይ የቢራ መስሪያ ንጥረ ነገሮች ብታምኑም ባታምኑም ከጠላ ጋር በጣም ይመሳሰላሉ። በዚህ አጋጣሚ አዲሱ ትውልድ ምግቡና መጠጡ ማን እንደሚሳራው እና በውስጡ ምን ምን እንደሚጨመር ለማወቅ ስለሚፈልግ የትላልቅ ቢራ አምራቾችን ቢራ ከመጠጣት ይልቅ የነዚህን ቢራ መጠጣቱ ለጤንነት ይጠቅማል ብሎ ስላሰቡ መሰለኝ የትጭው ብዛት አይጣል ነው.

Comments

Popular posts from this blog

Birhanu Nega scapped death

What company has copoun in Groupon

የአሜረካው ስታር ባክስ ኩባንያ በአሜሪካ ለሚገኙ ኢትዮጵያውን በነፍስ ወከፍ 50ሺ ዶላር ካሳ ለመክፈል ተስማማ