Wednesday, November 25, 2020

3200 KG drug used by a TPLF was seized

የትህነግ ዘራፊ ቡድን ሲጠቀምበት የነበረ 32 ኩንታል አደንዛዥ እፅ በቁጥጥር ስር ዋለ

**************** 


የትህነግ ዘራፊ ቡድን ሲጠቀምበት የነበረ 32 ኩንታል ካናቢስ የተሰኘ አደንዛዥ እፅ በቁጥጥር ስር ውሏል። 


አደንዛዥ እፁ በተሽከርካሪ ተጭኖ ከሁመራ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ሊገባ ሲል መያዙን የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ቴዎድሮስ ብርጌድ ዋና አዛዥ ኮማንደር ዘለቀ ምትኩ ተናግረዋል። 


በዓለም አቀፍ ህግ የተከለከለውን እፅ የትህነግ ዘራፊ ቡድን እድሜያቸው ለጦርነት ያልደረሱ ህፃናት እንዲጠቀሙት በማድረግ ወደ ጦርነት እያስገባቸው መሆኑን እጃቸውን የሰጡ የትህነግ የልዩ ኃይል አባላት መናገራቸውን ዋና አዛዡ ገልጸዋል።


ዘራፊ ቡድኑ ህፃናትን ወደ ጦርነት ማስገባቱ ሳያንስ ዓለም አቀፍ ወንጀል የሆነውን አደንዛዥ ዕፅ ህፃናት እንዲጠቀሙ ማድረጉ የወረደ ተግባር ማሳያ ነው ብለዋል።

 

ከአደንዛዥ እፁ በተጨማሪ ህገወጡ ትህነግ በአልመዳ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ያመረታቸው የፌዴራል ፖሊስ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የማረሚያ ቤት ፖሊስ አልባሳት አብሮ በቁጥጥር ስር መዋሉን ኮማንደር ዘለቀ ተናግረዋል ሲል አብመድ ዘግቧል። 


A 3200/KG  drug used by a gang was seized


 ***********

 Thirty-two quintals of cannabis used by the gang were seized


 Commander of the Amhara Regional State Special Forces, Tewodros Brigade Commander, Zeleke Mitiku, said the drug was seized on its way to Humera.




 According to the Commander-in-Chief, members of the TNG Special Forces have surrendered to the use of the drug, which is banned by international law.




 He said the gang's involvement in the war and the use of children as part of a global crime was an understatement


 In addition to the drug, federal police, the army and prison police uniforms produced by the illegal T-TPLF at the Almeda textile factory were also seized, Commander Zeleke said.

No comments:

Post a Comment