የቦ ታክስ

ለዲያስፓራ አባላት አሁን ኢትዮጵያ ላላችሁ። የአሜሪካ ታክሳችሁን ካላችሁበት ሆናችሁ እንድታሰሩ ነገሮችን ሁሉ አስተካክለናል። ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Back Tax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amendment), የዚህ አመት ታክስ እና ሌሎችንም እንሰራለን።በViber ሆነ Whatspp ይደውሉልን። 619 255 5530 ። YebboTax info@yebbo.com Yebbo.com

Monday, November 16, 2020

"የህግ ማስከበር ዘመቻው በጽንፈኛው የሕወሓት ጁንታ ላይ ብቻ ያተኮረ ነው"፡- የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት

"የህግ ማስከበር ዘመቻው በጽንፈኛው የሕወሓት ጁንታ ላይ ብቻ ያተኮረ ነው"፡- የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት
*****************

የእተከናወነ ያለው የህግ ማስከበር ዘመቻ በጽንፈኛው የሕወሓት ጁንታ ላይ ብቻ ያተኮረ እንደሆነ በዘመቻው ላይ እየተሳተፉ ያሉ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ተናገሩ።

ጽንፈኛው የሕወሓት ጁንታ ባለፉት ሁለት ዓመታት የተለያዩ ህገ ወጥ ድርጊቶችን በማቀነባበርና የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ ለበርካታ ዜጎች ህይወት መቀጠፍና መፈናቀል እጁ እንዳለበት በተደጋጋሚ ሲጠቀስ ቆይቷል።

መንግስት በትግራይ ክልል የመሸገውን ፅንፈኛ የሕወሓት ጁንታ ለሕግ ለማቅረብ እየወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ኢዜአ ያነጋገራቸው የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት እንደሚሉት፤ ሰራዊቱ ጽንፈኛ ቡድኑን ለህግ ከማቅረብ ባለፈ ማናቸውንም አይነት የውስጥና የውጭ ጥቃት የመመከት ቁመና ላይ ይገኛል።

ይህን አቅሙን በመጠቀምም በትግራይ ክልል የመሸገውን የሕወሓት ጁንታ ለህግ ለማቅረብ የህግ ማስከበር ተግባር እየተከናወነ መሆኑንም ነው ያስረዱት።

ህግ ማስከበሩ ስራ በትግራይ ስም በመሸገው ህገ ወጥ ቡድን ላይ ብቻ ያተኮረ እንጂ በቡድኑ ጭቆና ስር የነበረውን የትግራይ ህዝብ እንደማይመለከት ነው የሚናገሩት።

ከዚህ አንጻር መከላከያ ሰራዊቱ ከወገኑ የትግራይ ህዝብ ጋር ያለው አብሮነት ተጠናክሮ የሚቀጥል ስለመሆኑ አረጋግጠዋል።

የህግ ማስከበሩ ስራ የትግራይን ህዝብ ከጭቆና እና አፈና ነጻ የሚያወጣ በመሆኑ የክልሉ ነዋሪ ከመከላከያ ጎን በመሆን እያከናወነ ያለውን ድጋፍና እገዛ እንዲያጠናክር ጥሪ አቀርበዋል።


No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

Curated Products for Generation X

https://amzn.to/3VhbwJz GenX Essentials - Curated Products for Generation X ...

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon