የቦ ታክስ

ለዲያስፓራ አባላት አሁን ኢትዮጵያ ላላችሁ። የአሜሪካ ታክሳችሁን ካላችሁበት ሆናችሁ እንድታሰሩ ነገሮችን ሁሉ አስተካክለናል። ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Back Tax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amendment), የዚህ አመት ታክስ እና ሌሎችንም እንሰራለን።በViber ሆነ Whatspp ይደውሉልን። 619 255 5530 ። YebboTax info@yebbo.com Yebbo.com

Thursday, November 19, 2020

የህወሃት ቡድን በትግራይ ክልል በንጹሃን ዜጎች ላይ መድፍ በመተኮስ ጥቃት እየፈጸመ ነው

የህወሃት ቡድን በትግራይ ክልል በንጹሃን ዜጎች ላይ መድፍ በመተኮስ ጥቃት እየፈጸመ ነው
********************************
የህወሓት ቡድን በትግራይ ክልል በንጹሃን ዜጎች ላይ መድፍ በመተኮስ ጥቃት እየፈጸመ መሆኑ ተገለጸ።

በአገር መከላከያ ሠራዊት የሚደርስበትን ጥቃት መቋቋም ያቃተው የህወሓት ቡድን ከሰሜን ዕዝ የሰረቃቸውን ታንኮች ጥሎ መሄድ መጀመሩ ተገልጿል።

በደቡብ ዕዝ የሰው ሃብት ልማትና ሚዲያ አስተባባሪ ኮሎኔል ደጀኔ ጸጋዬ እንዳሉት ዘራፊው የህወሓት ቡድን የመከላከያ ሠራዊቱን መቋቋም ተስኖታል።

በዚህም ከሰሜን ዕዝ የሰረቃቸውን ሁለት ቲ-72 ታንኮችና ሌሎችም ቁሳቁሶቹን እየጣለ ሸሽቷል ብለዋል።

ለእኩይ ዓላማ የተሰለፈው ይህ ቡድን የመከላከያ ሠራዊቱን በትር መቋቋም ሲሳነው በንፁሃን ዜጎች ላይ መድፍ በመተኮስ ጥቃት እያደረሰ መሆኑን ገልጸዋል።

የመከላከያ ሠራዊት በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ነዋሪዎች በደስታ ስሜት እየተቀበሉን ነው ብለዋል።

የህወሓት ቡድን መጨረሻው እየደረሰ መሆኑን የገለጹት ኮሎኔል ደጀኔ ከመሸገበት አውጥቶ ለሕግ ለማቅረብ በሂደት ላይ መሆኑን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ቀደም ብለው ቡድኑ በሶስት ቀናት ውስጥ በሠላም እጁን እንዲሰጥ የጊዜ ገደብ ማስቀመጣቸው ይታወሳል።

Via EBC

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

Curated Products for Generation X

https://amzn.to/3VhbwJz GenX Essentials - Curated Products for Generation X ...

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon