ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩ ግጭቶችን አስመልክተው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች:-
************************
• በእያንዳንዱ ሳምንት የጦርነት ድግስ ነበር፣ መንግስት ስራ እንዳይሰራ በየቦታው ችግር ይፈጠር ነበር፣ 113 የሚሆኑ ግጭቶች ተፈጥረዋል፡፡
• የብሔር፣ የሃይማኖት ግጭት እንዲነሳ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡
• አንድ ጎጃሜ ከጎጃም ወደ አምቦ ሲሄድ ወገኔ ነው ብሎ ነው የሚሄደው፣ ይህ ህዝብ በጥርጣሬ እንዲታያይ ነው ለማድረግ የሞከሩት፡፡
• ባለፈው ሁለት ዓመት ተኩል በኦሮሚያ ውስጥ 37 ግጭቶች ነበሩ፡፡
• ባለፈው ሁለት ዓመት ተኩል በአማራ ክልል 23 ግጭቶች ነበሩ፡፡
• በአማራ ክልል ቅማንት የወሰድን እንደሆነ ጎንደር ከሁሉም ብሔሮች ጋር አብሮ ለመኖር ልምድ ያለው አከባቢ ነው፣ ቅማንትና አማራ ተብሎ መለየት በማይቻል ደረጃ ነው የህዝቡ አኗኗር፡፡
• በቤንሻንጉል ጉሙዝ 15 ግጭቶች ተከስተዋል፡፡
• አዲስ አበባ ላይ 14 ግጭቶች ተከስተው ነበር፡፡
• የሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን በተመለከተ ከሃጫሉ በተጨማሪ ሌሎች የኦሮሞና የአማራ አመራሮችን በመግደል ግጭቱን የኦሮሞና የአማራ ለማስመሰል ጥረት ተደርጓል፡፡
• ከዚያ በኋላ ሃጫሉን አጥተናል እና ሌሎች ጉዳቶች እንዳይደርሱ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡
• በጋምቤላ 7 ግጭቶች ነበሩ፡፡
• በሚዛን ቴፒ፣ ጉራፈርዳ ግጭቶች ተከስቷል፡፡
• ጉጂና ጌዲዮ እንደ አንድ ቤተሰብ የሚኖር ህዝብ ሲሆን፣ እዚያ አካባቢ ሰዎች እንዲፈናቀሉ ተደርጓል፡፡
• አማራ ክልል፣ ቤኒሻንጉል ያዋስነዋል ተጋጭቷል፣ ኦሮሚያ ያዋስነዋል ተጋጭቷል፣ አፋር ያዋስኗል ተጋጭቷል፣ ትግራይ ያዋስነዋል ነገር ግን አልተጋጨም፡፡
• ሌሎች ክልሎችም ከጎረቤት ክልሎች ጋር እንዲጋጩ ተደርጓል፣ ትግራይ ክልል ጎረቤት ክልል ቢሆንም ከትግራይ ግን አለመጋጨታቸው ግጭቱ ታስቦበት የሚሰራ በመሆኑ ነው፡፡
No comments:
Post a Comment