Call Yebbo

YebboTax Ethiopian Banner
ለአሜሪካ ታክስ ከፋዮች፣ አመታዊ ታክሳችሁን፣ ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Backtax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amdment) ካላችሁ የትም ሆናችሁ ማሰራት ትችላለችሁ።የኢትዮጵያ ፓስፖርት፣ የቢጫ ካርድ፣ ውክልና፣ የትርጉም ስራ ይፈልጋሉ? በViber/WhatsApp በ619 255 5530 ደውሉልን። info@yebbo.com Yebbo.com

Saturday, November 14, 2020

በአዲስ አበባ ከተማ በማንኛውም ምክንያት ርችት መተኮስ የተከለከለ መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ

በአዲስ አበባ ከተማ በማንኛውም ምክንያት ርችት መተኮስ የተከለከለ መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ
*****************

በአዲስ አበባ ከተማ በማንኛውም ምክንያት ርችት መተኮስ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

አንዳንድ ግለሰቦችና ተቋማት ልዩ ልዩ ፕሮግሞችን ምክንያት በማድረግ  ርችት እየተኮሱ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት ሀገሪቷ ካለችበት የፀጥታ ሁኔታ አንፃር በምንም አይነት ምክንያት ርችት መተኮስ የተከለከለ መሆኑን ነው ፖሊስ ያሳሰበው።

ፖሊስ ኮሚሽኑ ሕግን የማስከበር ስራውን አጠናክሮ መቀጠሉን እና ህብረተሰቡም ለኮሚሽኑ ስራ ስኬታማነት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጿል።

መልእክቱን በመተላለፍ ርችት ሲተኩስ የተገኘ ግለሰብ በህግ የሚጠየቅ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በጥብቅ አሳስቧል።
  
ህብረተሰቡ ለህግ መከበር እያደረገ ላለው ቀና ትብብር ኮሚሽኑ ምስጋናውን አቅርቦ ትብብሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አስተላልፏል።


No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon