Call Yebbo

YebboTax Ethiopian Banner
ለአሜሪካ ታክስ ከፋዮች፣ አመታዊ ታክሳችሁን፣ ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Backtax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amdment) ካላችሁ የትም ሆናችሁ ማሰራት ትችላለችሁ።የኢትዮጵያ ፓስፖርት፣ የቢጫ ካርድ፣ ውክልና፣ የትርጉም ስራ ይፈልጋሉ? በViber/WhatsApp በ619 255 5530 ደውሉልን። info@yebbo.com Yebbo.com

Monday, November 16, 2020

ጀግናው አየር ሃይል ስለደመሰሰው ሚሳይል

መረጃ
ጀግናው አየር ሃይል ስለደመሰሰው ሚሳይል
[ S-125 SA-3 GOA ]
ትህነግ ለሽብር ጥቃት ያዘጋጀችው ሚሳይል ሲስተም ትናንት በአየር ሃይላችን መደምሰሱ ይታወሳል። የእስራኤል ወታደራዊ ዌብሳይትም ሳይቱን ይፋ አድርጓል። ጥቂት ስለ ሚሳይሉ...
ራሺያ ሰራሽ ነው። በመካከለኛ የከፍታ ወለል ላይ ከምድር ወደ አየር የሚተኮስ ሚሳይል ሲስተም፤ Accuracy ው 650 ሜትር፤ እንደ ሲስተሙ ሁኔታ ከ 200 ኪ.ሜ በላይ ይጓዛል።
S-125 ሚሳይል ለተኩስ ሲዘጋጅ እስከ 90 ° የሚሽከረከር አራት ማዕዘን ቦርድ ዝግጅቱን ያስጀምራል። አራት የ 2.6 ሰከንድ የዝግጅት ማቀጣጠያ ቆይታ ያላቸው ክፍሎች ያሉት። ለጉዞ ማራዘሚያ ዘላቂ ሞተር የተገጠመለት፤ አራት አራት ቀጥ ያሉ ክንፎችና አራት ወደፊት ተንቀሳቃሽ መቆጣጠሪያ አለው ፡፡ ሚሳኤሉ ከበስተኋላ ክንፎቹ ላይ ወደ አንቴናው ከሚላከው guiding ምልክቶች የሲስተም ራዳር ክትትል ይደረግበለል፡፡ 2 የተለያዩ ሚሳይሎችን ይጠቀማል።
S-125 ከፊል ተንቀሳቃሽ ነው፣ ሚሳኤሎቹ በሁለት ወይም አራት ቋሚዎች ይተከላሉ። በ ZIL መኪናዎች ላይ ሲሆን ጥንድ ጥንድ ሆነው ለተልዕኮ ሊዘጋጁ ይችላሉ ፡፡
የታጠቁት አገራት
ኢትዮጵያ [የተወሰነው በጁንታው ዕጅ] ፣ሰሜን ኮሪያ፣ ሩሲያ፣ ግብፅ፣ ሕንድ፣ አዘርባጃን፣ አልጄሪያ፣ አንጎላ፣ አርሜኒያ፣ ቡልጋሪያ፣ በርማ፣ ካምቦዲያ፣ ቼክ ሪፐብሊክ፣ ኩባ፣ ፊንላንድ፣ ፖላንድ፣ ሶማሊያ፣ ዩክሬን፣ ታንዛኒያ፣ ቬትናም እና ሌሎችም ይገኛሉ።

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon