የቦ ታክስ

ለዲያስፓራ አባላት አሁን ኢትዮጵያ ላላችሁ። የአሜሪካ ታክሳችሁን ካላችሁበት ሆናችሁ እንድታሰሩ ነገሮችን ሁሉ አስተካክለናል። ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Back Tax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amendment), የዚህ አመት ታክስ እና ሌሎችንም እንሰራለን።በViber ሆነ Whatspp ይደውሉልን። 619 255 5530 ። YebboTax info@yebbo.com Yebbo.com

Monday, January 3, 2022

Attaye High School began teaching and learning

የአጣዬ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመማር ማስተማር ሥራ ጀመረ
****************** 

በአሸባሪ ህወሓት በኦነግ ሸኔ ከፍተኛ ገዳት የደረሰበት የአጣዬ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራውን መጀመሩን የትምህርት ቤቱ ሱፐርቫይዘር አስታወቁ። 

የትምህርት ቤቱ ሱፐርቫይዘር አቶ ማሙሽ ሲከፋኝ ትምህርት ቤቱ አንጋፋ እና በክልሉ ካሉ ውጤታማ ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ነገር ግን በጥፋት ኃይሎች በተደጋጋሚ የጉዳት ሰለባ በመሆኑ በትምህር ቤቱ ላይ ከፍተኛ ውድመት መድረሱን አስታውሰዋል። 

የትምህርት አስተዳደሩ በደረሰው ጉዳት ተስፋ ሳይቆርጥ የአጥፊ ቡድኖቹ  ዕቅድ እንዳይሳካ ትምህርት ለማስጀመር ከመምህራን ጋር ተግባብቶ የማስተማር እንቅስቃሴ መጀመራቸውንም ገልፀዋል። 

የትምህርት ቤቱ መምህራን በበኩላቸው ካለው ጫና ተላቅቀው በቀረው ትንሽ የትምህርት ግብዓት የመማር ማስተማር ሥራውን በተሻለ የሥነ-ልቦና ዝግጅት መጀመራቸውንም ተናግረዋል። 

ከዚህ በተጨማሪም የትምህርት ቤቱ መምህራን ትምህርት ቤቱን ከማፅዳት ጀምሮ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ሙሉ በሙሉ እንዲመጡ ሥነ-ልቦናቸውን የመገንባት ሥራም እየሠሩ እንደሚገኙ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። 

የተለያዩ አካላት ችግሮቹን መጥቶ ከመመልከት በዘለለ የመማር ማስተማር ሥራውን ውጤታማ ለማድረግ ከመንግሥት ጀምሮ ሁሉም የሚችለውን ድጋፍ እዲደረግ የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ጠይቋል።
Attaye High School began teaching and learning
 ******************

 Attaye High School, which was severely damaged by the OLF, has resumed its regular teaching and learning activities, according to the school's supervisor.

 The school's supervisor, Mamush, said the school was one of the oldest and most successful schools in the region, but that the school had been severely damaged by the forces of destruction.

 He also said that the education administration has not given up on the damage done by the destructive groups.

 The teachers of the school, for their part, said that they are relieved of the burden and have started the work of teaching and learning with a better psychological preparation.

 In addition, information from the Ministry of Education indicates that the teachers are working to improve the morale of the students, starting with cleaning the school.

 The school administration has called on the government to do all it can to make the teaching and learning process more effective.


No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

Curated Products for Generation X

https://amzn.to/3VhbwJz GenX Essentials - Curated Products for Generation X ...

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon